ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ አባል እንድትሆን የሚገለፅ በፅሁፍ የተዘጋጀ ደብዳቤ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማቅረቡን ገለፀ!
ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ አባል እንድትሆን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ከአረብ ሊግ ተጠባባቂ ፀሐፊ ጋር በነበረው ውይይት የኢትዮጵያ መንግስት ጥያቄውን በይፋ ካቀረበ ምላሽ እንደሚሰጡ በገለፁት መሠረት በጽሑፍ የተዘጋጀውን ደብዳቤ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ጊዲዮን ጢሞቲዬስ መሰጠቱ ተገለፀ።
ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ጊዲዮን ጢሞቲዬስ በ17/03/2017 በጽ/ቤታቸው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ክቡር ዶ/ር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ተቀዳሚ ም/ፕሬዝዳንት ሸይኽ አብድልከሪም ሸህ በድረዲን፣ የጠቅላይ ም/ቤቱ ዋና ፀሐፊ ሸህ ሃሚድ ሙሣ እና የጠቅላይ ም/ቤቱ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ የሆኑት ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ጋር በተያዘው ቀጠሮ መሠረት በመገናኘት ሰፊ ውይይት መደረጉ ተነስቷል።
በተደረጉት ውይይቶች የተነሱ ዋና ዋና ጉዳዩች 5 ሲሆኑ፡-
1. ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ አባል እንድትሆን በጠቅላይ ም/ቤቱ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ከአረብ ሊግ ተጠባባቂ ፀሐፊ ጋር በነበረው ውይይት የኢትዮጵያ መንግስት ጥያቄውን በይፋ ካቀረበ ምላሽ እንደሚሰጡ በገለፁልን መሠረት በጽሑፍ የተዘጋጀውን ደብዳቤ ለክቡር ሚ/ሩ መቅረቡ
2. በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና መ/ቤትና በተለያዩ አገራት በተመደቡ ዲፕሎማቶች ዙሪያ የሙስሊሙ አካታችና አሳታፊነት ምን እንደሚመስል? ለማካተትስ ምን እየተሰራ ነው? የሚለው ጥያቄ
3. በፌዴራል መንግስት አዋጅ ቁጥር 1207/2012 ለጠቅላይ ም/ቤቱ በተሰጠው ስልጣን መሠረት በውጭ አገር ቅርንጫፍ ቢሮዎችን የመክፈት እና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውዮን ሙስሊሞች የሚያቋቁሙት ጽ/ቤቶች ለመክፈት እንዲያስችላቸው በውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስፈላጊውን እገዛና ትብብር እንዲያደርግላቸው።
4. በሳዑዲ አረቢያ ጅዳ ከተማ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ውስጥ የሐጅና ዑምራ ጉዳይ የሚያስተባብርና የሚከታተል ዲፕሎማት እንዲሾምልን ከዚህ በፊት ለነበሩ 2 ሚኒስትሮች ጥያቄው ቀርቦ ምላሽ ያላገኘ ሲሆን አሁን ካስፈላጊነቱ እንፃር ተገንዝበው ተወካይ እንዲመደብ የሚጠይቅ።
5. ከላይ የተጠቀሱትን ጥያቄዎች አፈፃፀም ላይ ሁሌም ስለምንቸገር ከሚ/ር መ/ቤቱና ከጠቅላይ ም/ቤቱ ጋር በጋራ የሚሰሩ ተወካዮች እንዲመደቡ በየእለቱ በመገናኘት እንዲያስፈጽሙ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል እና በጠቅላይ ም/ቤቱ በኩል ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ተመድበው ስራዎች እንዲያከናውኑ ስምምነት ላይ መደረሱም ነው የተገለፀው
በአጠቃላይ በነበረው ውይይት አዎንታዊ ምላሽ የተሰጠ ሲሆን ውጤቱን በቀጣይ በመጠባበቅ ለህዝቡ ሙስሊሙ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን ሲል የኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አሳውቋል፡፡




10 comments
ለምን ግን የኔቶ አባልም አንሆንም ግን
የኔቶ ና ደግሞ የምዕራብ ሀገራት ህብረትም መቀላቀል አለብን 😂
ኢትዮጵያ የሙስሊም ሀገረ ለማድረግ ሴራ ብቆም ጥሩ ነዉ ፡፡
ከወቅታዊ አቋማችን ማይሻል ነገር የለም መቸም
ይሄ ሁሉ የኤምሬቶች እግር መላስ መጨረሻው እኮ የታወቀ ነው።
ሰዉ ለሚመጣው ቢዘጋጅ ነው ሚሻለው፡፡
ጥያቄው የኢትዮጵያ ወይስ የእልምና ጉዳይ ም/ቤት መሆን አለበት?
ጥያቄው ፖለቲካዊ ወይስ ሀይማኖታዊ መሆን አለበት?
የኢትዮጵያ የመሀይምነት ጥግ እኮ ደስ ይላል….
ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት አረብ አይደለችም እስላምም አይደለችም ከተቀበሉት ግን መዘዙ ከባድ ነው ቀስ እያለ በሸሪአ ሁሉም ”ብሔር ብሔረሰቦች” ይተዳደራሉ ወደ ማይቀረው እየሄድን ነው
ሮላንዶ የሚወዳደርበትን ሊግ ከምንመኝ መጀመሪያ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን በስነስርአት ብንወዳደር አይሻልም 🤣
አረብ፡አይደለንም፡ሀበሻ፡ነን፡፡፡
ለምን ቀድመን የአውሮፓ ህብረት አንቀላቀልም? ጂኦግራፊ ካልጠየቀ!