banner

በወርቅ ሥርቆት የተጠረጠሩ የፖሊስ አዛዥ ተያዙ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን ሦስት ኪሎ ግራም ጥፍጥፍ ወርቅ በመሥረቅ የተጠረጠሩ የወረዳ ፖሊስ አዛዥ ታሠሩ ፡፡ በዞኑ የጮርሶ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ በቁጥጥር ሥር የዋሉት በኮትሮባንድ ሲዘዋወር ከተያዘው ሰባት ኪሎ ግራም ጥፍጥፍ ወርቅ መካከል ሦስቱን ወደ ቤታቸው ይዘው በመሄዳቸው ነው ተብሏል ፡፡ አዛዡ ወርቁን ወደ ቤታቸው መውሰዳቸው ሊታወቅ የቻለው ወርቁን ሲያዘዋውሩ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሰዎች የተያዘብን ወርቅ ይሄ ብቻ አይደለም በሚል የሰጡትን ጥቆማ መሠረት በማድረግ በተካሄደ ምርመራ መሆኑን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አዛዣ ኮማንደር ግርማ በየነ ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል ፡፡

“ የጎደለ ወርቅ ሥለመኖሩ መረጃው እንደወጣ ተጠርጣሪው አዛዥ ከአካባቢው ለመሰወር ሞክረዋል ያሉት የመምሪያው አዛዥ “ ነገር ግን ፖሊስ ባለቤታቸውን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ አድርጓል ፡፡ የተጠርጣሪው አዛዥ ባለቤትም የቅርብ ዘመዶቻቸው ጋር በመደወል ወርቁን ከቤት በማስመጣት ገቢ አድርገዋል ፡፡ ተሰውረው የነበሩት አዛዥም ትናንት ሰኞ በሀዋሳ ከተማ ውስጥ በቁጥጥር ሥር ለማዋል ተችሏል “ ብለዋል ፡፡

በቀጣይ የወርቅ አዘዋዋሪዎችን እና ወርቁን ለመሰወር በሞከሩት የፖሊስ አዛዥ ላይ ተጨማሪ ምርምራ በማድረግ ለህግ የማቅረብ ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝም አዛዡ ጨምረው ገልጸዋል ሲል ዶቼ ቬለ ነው ያስነበበው።

9 comments

Diode Daniel November 26, 2024 - 7:11 pm

አጋጣሚውን አግንቸ በሰረኩትና famous አሆን ነበር

Reply
Workineh Becho Hidoto November 26, 2024 - 7:12 pm

መንግስት አሁን የትኛውን ወንጀለኛ ይቆጣጠር?🤔🙆

Reply
Lili Ye Su November 26, 2024 - 7:12 pm

እዶንም ተሸጦ ድርሻቸው ይሰጣቸው 🥴

Reply
Kibrom Tesfamariam November 26, 2024 - 7:13 pm

ለምን ? ፖሊሱ ከሰረቀ የፖሊሱን ባለቤት ለምን ትታሰራለች ምን ዓይነት ህግ ነው

Reply
Um Amita November 26, 2024 - 7:13 pm

ኸረ በስማም ቢስሚላ 😭😂😂😂

Reply
Abel Abel November 26, 2024 - 7:13 pm

ታዲያ ደመወዝ ይጨመራቸዋ
ምን ያድርጉ ✍️

Reply
Mesay Gashahun November 26, 2024 - 7:13 pm

እሽ አሁንን ሌባና ፖሊስ ነው ምባለው ፖሊስ ሌባ ሌባው ፖሊስ ነው የምንለው የኑሮ መጠረሪ እኮ ክፉ አረገን ጎበዝ

Reply
Tofa Máň Ĵŕ November 26, 2024 - 7:16 pm

አሉ ደሞ አንዳንድ ህጋዊ ሌቦች🙄

Reply
Mesay Gashahun November 26, 2024 - 7:16 pm

ሌቦች ደስ ይበላችሁ ፖሊስ ጎደኛችሁ ነው

Reply

Leave a Comment