banner

ሀሰተኛ ፈጣን ሎተሪ ደርሶኛል በሚል የማጭበርበር ወንጀል የፈፀሙ ሁለት ግለሰቦችን መያዛቸዉን ፖሊስ ገለፀ።

የቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር አዳነ አለማየሁ እንደገለፁት በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር አማን ቀበሌ ህዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 4:00 ሰዓት ሁለት ግለሰቦች ሆነዉ ሀሰተኛ ፈጣን ሎተሪ በመያዝ የግል ተበዳይዋን አማን ገበያ ላይ አግኝቷት የቢንጎ ሎተር ወጥቶልን በሚል ከባንክ 48,000፣ የእጅ ሞባይሏን፣የአንገት ወርቋን፣የጣት ቀለበቷን እና ወርቋን የጆሮ ወርቋን መዉሰዳቸዉን አስረድተዋል።

ግለሰቧን ምን እንዳስነኳት አለመታወቁን ያመለከቱት ፖሊስ አዛዡ ግለሰቧ ከ30 ደቂቃ በኋላ እንደተጭበረበረች ስለተረዳች ለፖሊስ በሰጠችዉ መረጃ ፖሊስ ተከታትሎ ሁለቱን ተጠርጣሪዎች ከ47,000፣የግል ተባዳይዋ የአንገት፣ የጣት፣የጆሮ ወርቅ እና ቴች ሞባይሏ ጋር በቁጥጥር ስር ዉለዉ ምርመራ እየተጣራባቸዉ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በመጨረሻም ምክትል ኢንስፔክተር አዳነ በሚዛን አማን ከተማ በተደጋጋሚ ጊዜ የሎተሪ ማጭበርበር ወንጀሎች እየተበራከተ በመሆኑ ህብረተሰቡ በመሠል አጭበርባሪዎች እንዳይታለል ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል ሲል የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን ዘግቧል።




1 comment

Agegnehu Mitiku Gebre December 5, 2024 - 2:42 pm

አንበሳ ፖሊስ ማለት ይሄ ነው

Reply

Leave a Comment