banner

ለአዲሶቹ አመራሮቻችን፥

ከአቤል ገ/ኪዳን የፈረንሰይ ለጋሲዮን ክለብ ምክትል ፕሬዝዳንት

እንግዲህ ከተመረጣችሁ ዘንዳ የማውቃቸውን አንዳንድ ጥያቄዎች ልጠይቃችሁና ላስመረጧችሁ ሰዎች አድርሱልኝ

1) የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ከሆናችሁ ዘንድ እግር ኳስ ወደ አዲስ አበባ ስቴድየም መቼ ነው ሚመለሰው ሚለውን ብትጠይቁልን? ቡና እና ጊዮርጊስ ወደሜዳቸው ተመልሰው የቀደመው ሙቀት እንዲመለስስ ክለቦቹን ለማገዝ ፍላጎት አለ ወይ? ወይስ ዘንድሮ እንደተደረገው የአዲስ አበባ ክለቦች የሌሉበት የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ ማካሄድ ነው ወይ አላማችሁ?

2) የቀደመው ፌደሬሽን ጣራ ላይ ሰቅሎት የሄደው የውድድር መመዝገቢያ ክፍያ ዝቅ አድርጋችሁ የአዲስ አበባ ልጆች ወደ ውድድር እንዲመለሱ ለማድረግ ምን እቅድ አላችሁ? (ካቻምና እኛ 15ሺ ከፍለን በ26 ክለብ የተወዳደርንበት ውድድር አምና ፌደሬሽኑ ክፍያውን በ300 እጥፍ በመጨመሩ የተሳታፊ ክለብ ከ26 ወደ 5 ወርዶ ብዙ የታዳጊ ክለቦች እንዲበተኑ መደረጉ የሚታወቅ ነው)

3) አበበ ቢቂላ ስቴድየም የአዲስ አበባ ክለቦች ውድድርን ገለል እያረገ እንደ ሆቴል ብር ለከፈለ ብቻ መከራየቱ ሚቆመው መቼ ነው?

4) ኳስ ክብ ይሁን አራት ማእዘን የማያውቁ ሰዎች በፌደሬሽኑ ቢሮ ውስጥ ተሰግስገው ታዳጊዎችን ማማረር የሚያቆሙት መቼ ነው?

5) የአዲስ አበባ የሰፈር ውስጥ ውድድሮች እንደ ስጋት ምንጭ ሳይታዩ በየአካባቢው በድምቀት እንዲካሄዱ ለማስቻል ውድድሮችን ለማገዝ ፍላጎት አለ ወይ?

ለጊዜው ይሄ ይበቃኛል!! የቀረውን ደሞ ወደፊት እጠይቃለሁ!!

10 comments

ኤርያድ ህገኛው December 5, 2024 - 7:06 pm

ወሰንሰገድ ገብረኪዳን 😥😃

Reply
ነገን ላዮው እጓጓለው December 5, 2024 - 7:07 pm

ኣገራቀፍ ፕራንክ ነው ኣደል

Reply
Mube Munis December 5, 2024 - 7:08 pm

እስጢፍ እና ጆን የታሉ

አስረግጬ ነው የምነግርህ ተጭበርብሯል 🥹🥹😂

Reply
Jere Miah December 5, 2024 - 7:09 pm

አዳዲሶቹ አመራሮች የብሄራዊ ቡድኑን ጎል የማስቆጠር ችግር ይቀርፋሉ ተብሎ ይጠበቃል…🙄

Reply
Ones Love December 5, 2024 - 7:09 pm

እሱም እኮ ድምፃዊ ነው 😭🤣🤣

Reply
Mr-x December 5, 2024 - 7:10 pm

ሞቶ የነበረውን የአገራችን እግር ኳስ ቀብር ለማስፈጸም ስለተመረጣችሁ እንኳን ደስ አላችሁ

Reply
Ermi Keyo December 5, 2024 - 7:11 pm

ኳስ እና ዱባ መለየት የማይችሉ ሰዎች ፌደሬሽኑን ይምሩ ማለት ለኳስ ወዳዶቹ ኢትዮጲያዊያን ትልቅ ንቀት ነው ያሳዝናል ከድጡ ወደ ማጡ አለ የሀገሬ ሰው።

Reply
KE N ZU December 5, 2024 - 7:11 pm

አቤል ማስቲን ባታስጨንቅብን ምን ይመስልሀል?🙄😇

Reply
Yetnayet Endale December 5, 2024 - 7:13 pm

ታዋቂ መሆን ብቻ በቂ ነው ማለት ነው ለመምራት እኮ ቢያንስ ትንሽ ቅርበት መኖር አለበት!!የተመረጡት ሰዎች እግር ኳስን በቅጡ ይወዳሉ የሚለው ላይ ጥርጥር አለኝ!!

Reply
Beti Fantaye December 5, 2024 - 7:15 pm

ጎል ሲገባብን ጌታ ይባረክ ሃሌሉያ ልንል ነዋ😂😂😂😂😂😂

Reply

Leave a Comment