0
የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ዛሬ ባደረገው ስብስባ አዲስ ተመራጭ ስራ አስፈፃሚ የአርቲስት ሀረገወይን አሰፋን ጥያቄ ተቀብሎ በሌላ ሀላፊነት መመደቡ ታውቋል።
አርቲስት ሀረገውይን የስራ መደራረብ ስላለበኝ ከአቃቤ ነዋይነት ሌላ ሀላፊነት ስጡኝ ብላ ያቀረበችው ጥያቄ ተቀባይነት በማግኘቱ በአዲሱ ስራ አስፈፃሚ የማርኬቲንግ ሀላፊው የአቶ ኢሳያስ ተፈሪ ምክትል ሆና እንድትሰራ ተመድባለች።
በአርቲስት ሀረገወይን አሰፋ ምትክ የአቃቤ ነዋይ ቦታን ወ/ሮ አሰፋሽ ታገሰ ተክታ እንድትሰራ መመደቧ ተረጋግጧል ።
ምክትል ፕሬዝዳንት ተዋናይነት ማስተዋል ባለችበት ስራዋን እንድትቀጥልም ስራ አስፈፃሚው ወስኗል።
Via: ባላገሩ ስፖርት

4 comments
እኔ እኮ የማስተዋል confidence ነው ሚገርመኝ
እና እኛን ምን አድርጉ ነው የምትሉን
ለዚህ ስራ የሚመጥን ሰው ጠፍቶ ነው ግን አርቲስቶች የተመረጡት እነሱ ቦታ ላይ ለመሆን ጥበብን ትወናን ይገመግማሉ እዚህ ትልቅ የሀላፊነት ቦታ መቀመጥ ያለባቸው አሰልጣኞች አንጋፋ ተጫዋቾች ለምን አይመረጡም ኳስ እንኳን ለማይደግፍ ሰው ይህን ሀላፊነት መስጠት አርሰናል ማነው ሲባል ገበሬው ነው እንደማለት ይቆጠራል ማስተዋል ማስተዋሉን ይስጥሽ
Yichi Hager endew ye manm mechawecha hona tiker yemigerm nw😑😑😑😑