የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመዉ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ካፋ ዞን ውስጥ ሲሆን ወንጀሉን የፈፀሙት ሶስት ግለሰቦች መሆናቸዉን ታዉቋል።
አንደኛ ተከሳሽ አማኑኤል ማናለ ማሞ፣ሁለተኛ ተከሳሽ አስራት አክሊሉ ደምሴ እና ሶስተኛ ተከሳሽ ታድዮስ ተስፋዮ ተሾመ የእስራት ቅጣቱ ሊወሰንባቸዉ የቻለዉ የተጫነ ዕቃን ካላወረድን በሚል የግል ተበዳይን ደብድበዉ በመግደላቸዉና ጥፋተኝነታቸዉ በማስረጃ መረጋገጡን የገለፁት በካፋ ዞን ፍትህ መምሪያ የልዩ ልዩ ወንጀሎች ዐቃቤ ህግ ዮናስ ተረፈ ናቸው፡፡
ተከሳሾቹ ሰዉ ለመግደል አስበዉ በካፋ ዞን አዲዮ ወረዳ ማጫ ቀበሌ የካቲት 15 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት በወረዳዉ ዳጊ ማጫ ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ አርብ ቀን በሚቆም ገበያ የግል ተበዳይ ባጃጅ ገብስ በኩንታል ጭኖ በማምጣት ለማዉረድ ሲል እኛ እያለን አታወርድም በሚል ወንጀሉን መፈፀማቸዉን ፖሊስ ምርመራዉ አረጋግጧል ብለዋል።
እንደ ዐቃቤ ህግ ዮናስ ገለፃ የአዲዮ ወረዳ ፖሊስ ሶስቱን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር አድርጎ ባደረገዉ ምርመራ ሁለተኛ ተከሳሽ የተጫነዉን ገብስ አወርዳለሁ ሲል የግል ተበዳይ የምከፍልህ ገንዘብ የለኝም አታወርድም በሚልበት ወቅት የግል ተበዳይን አንገቱን አንቆ ይዞ ደረቱ ላይ በእጅ ቦክስ ሁለት ጊዜ መምታቱ አስረድተዋል።
እንዲሁም ሶስተኛ ተከሳሽ ሁለት እጆቹን ይዞ ሽንጡ ላይ በእግሩ ደጋግሞ በመርገጥ አንደኛ ተከሳሽ ሆዱ ላይ በእግሩ በመርገጥ ከባድ ጉዳት ማድረሳቸዉንና ተጎጂዉ ማጫ ጤና ጣቢያ ቢወሰድም የደረሰበት ምት ከፍተኛ በመሆኑ ህይወቱ ማለፋን ነዉ በፖሊስ የምርመራ መዝገብ የተረጋገጠዉ መሆኑን ዐቃቤ ህጉ ጨምረዉ ተናግረዋል።
የወረዳዉ ፖሊስ ሶስቱ ወጣቶች የፈፀሙትን የወንጀል ድርጊት በሰዉ ምስክሮች እና በህክምና ማስረጃ የምርመራ መዝገቡን በማደራጀት ክስ እንዲመሠረትበት ለካፋ ዞን ፍትህ መምሪያ ዐቃቤ ህግ መዝገቡን ልኳል።
ዐቃቤ ህግ ከፖሊስ የደረሰዉን የምርመራ መዝገብ መነሻ በማድረግ ሶስቱን ግለሰቦች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 32 ንዑስ አንቀፅ 1 ሀ እና 540 ላይ የተደነገገዉ ተላልፎ በመገኘቱ ሰዉ መግደል ወንጀል ክስ መስርቶባቸዉ ፍርድ ቤት አቅርባቸዋል።
የካፋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዐቃቤ ህግ ሶስቱን ግለሰቦች ከሶ የቀረበዉ ክስ ግራ ቀኙን ሲያከራክር ቆይቶ ሶስቱንም ተከሳሾች በቀረበባቸዉ ማስረጃ መሠረት ጥፋተኞች ናችሁ ሲል የጥፋተኝነት ብይን ሰጥቷል።
በዚሁ መሠረት የካፋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለዉ የወንጀል ችሎት አንደኛ አማኑኤል ማናለ ማሞ፣ሁለተኛ ተከሳሽ አስራት አክሊሉ ደምሴ እና ሶስተኛ ተከሳሽ ታድዮስ ተስፋዬ ተሾመ እያንዳንዳቸዉ በ8 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ዉሳኔ አስተላልፎባቸዋል ሲል ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን ተናግረዋል።

10 comments
ሰውን ገለው 8 ዓመት ምን ያደርጋል ፣ አስተማሪ ሳይሆን የኢኮኖሚ ግሸበት በኋላ እንዲመለሱ ነው ።
እቺ ሃገር የማንም ማላገጃ ሆና ቀረች ኣ
ሰውን ደብድቦ ገሎ 8 አመት ብቻ አይከብድም ??
ቤተሰብን ያለ ጣሪ አስቀርቶ ለፍቶ አዳሪን ደፍተው አስቀርተው ????? አንዴ??
መላው ሀገሪቷ ለይ ያለ እና መላ የታጣለት ጉዳይ ሀይ ባይ የሌለው ህግ አውጪ መች ቸገረን ህግ አስፈፃሚ እንጂ😥
ወይ ኢትዮጵያ!!!!
የመኖር መብት እንኳን የሌለበት ሀገር!!!
በገዛ ንብረቱ ላይ!!!
ይህ ጉዳይ ሊታሠብበት ይገባል ወሬ ብቻ መሆን አያስፈልግም ደሞ ሰው ገሎ 8አመት????
Beyesusm yemaymeles yesewun hwoyt atfto 8 amet? fity wodet alesh?
ሟቹ ወንድም የለውም ሲወጡ ፍርዱን እሱ ይፍረድባቸው😭😭😭
3ቱን ገዳዮች ገድዬ 24 ዓመት ብቀጣ
Special Bonga $gesha be careful indaynet negr ale sidb dibdeba menarya wusxi y gesha simrtochi irasu bxenqequ