banner

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱሉልታ ወረዳ የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ለገሰ ሥዩም ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ በ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱሉልታ ወረዳ የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ለገሰ ሥዩም ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ በሚጠራው አማጺ ቡድን መገደላቸውን ዋዜማ ዘግባለች።

ከፖሊስ አዛዡ በተጨማሪ የወረዳው የብልፅግና ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ሲሳይ በሻዳ ተመትተው ጫንጮ ሆስፒታል መግባታቸውን ሰምተናል፡፡

በጥቃቱ ሁለት የመከላከያ ሠራዊት አባላትና አንድ የኦሮሚያ ፖሊስ አባል በድምሩ አራት ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን ዋዜማ ማረጋገጥ ችላለች።

አማጺ ቡድኑ ጥቃቱን የፈጸመው ዛሬ ታህሳስ 1 ቀን ጠዋት 3 ሰዓት አካባቢ ልዩ ስሙ ሮብ ገበያ በተባለ ስፍራ መሆኑን የገለጹት ምንጮች፣ ፖሊስ አዛዡና የጸጥታ ኃይሎቹ ወዲያው ሕይወታቸው ሲያልፍ፣ የብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊው ወደ ጫንጮ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ለዋዜማ አረጋግጠዋል።

አማጺ ቡድኑ <<የክልሉ መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተቀብለናል>> በማለት ቀድመው ማሳወቃቸውን ተከትሎ አመራሮቹና የጸጥታ ኃይሎቹ ወደ ስፍራው ማቅናታቸውን ምንጮች ጠቁመዋል።

ሆኖም በስፍራው ሲደርሱ በአማጺ ቡድኑ በኩል በተከፈተባቸው ድንገተኛ የእሩምታ ተኩስ የፖሊስ አዛዡና የጸጥታ አባላቱ ሕይወታቸው ማለፉት ምንጮች ተናግረዋል።

ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ከፈጸሙ በኋላ አመራሮቹ ሲንቀሳቀሱበት የነበረውን ፓትሮል ተሽከርካሪ አቃጥለው ከጥቅም ውጪ ማድረጋቸውንም ዋዜማ ሰምታለች።

አማጺ ቡድኑ ከዚህ ቀደምም የውጫሌ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪና ከሃምሳ በላይ የጸጥታ አባላትን መግደሉን ዋዜማ መዘገቧ የሚታወስ ሲሆን፣ ከአንድ ዓመት በፊትም የሱሉልታ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ በተመሳሳይ በታጣቂዎቹ መገደላቸው ተጠቁሟል፡፡

ድርጊቱ የተፈጸመው የክልሉ መንግሥት በቅርቡ ከአማጺ ቡድኑ አንድ ክንፍ ጋር አደረኩት ባለው የሠላም ስምምነት በርካታ የቡድኑ ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ ማዕከላት እየገቡ እንደሆነ እየተገለጸ ባለበት ወቅት ነው።

ዘገባው የዋዜማ ነው

8 comments

Esmael Abbaa Jabal December 10, 2024 - 7:43 pm

የቤተሰብ ጨዋታ አስመሰሉት እኮ 😁

Reply
አሐቲ አሐቲ December 10, 2024 - 7:45 pm

ሸገር የገቡትም ምናለ ውለታ ቢውሉልን 🫣

Reply
Dani Yishak December 10, 2024 - 7:45 pm

እንደፈለጉ እኛ በቤተሠብ መሀል አንገባም

Reply
ቲጂ ቲጂ December 10, 2024 - 7:45 pm

አረ ኡፍፍፍ ምን ይሻላል 🥺🥺💔

Reply
ፍቅር ፍቅር December 10, 2024 - 7:46 pm

እኛ በቤተሰብ ጉዳይ ጣልቃ አንገባም😏🤔

Reply
Kokeb December 10, 2024 - 7:46 pm

ገና መአት ታመጣላቹ😴😴😴

Reply
Mas Abawaji December 10, 2024 - 7:48 pm

አሳዛኝ ነው ነገሩ

Reply
አማራ ደመላሽ December 10, 2024 - 7:49 pm

ለበአሉ ማለትም ለቁማሩሩ ድምቀት ነው።😁

Reply

Leave a Comment