0
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦትና አገልግሎት ሐዋሳ ቅርንጫፍ አገልግሎቱን በቴክኖሎጂ በማዘመን ኢመርጀንሲ የሆኑ እና አንዳንድ የመንገድ ችግር በሚስተዋልበት ወቅት ለጤና ተቋማት ክትባቶችን ማድረስ የሚያስችል የድሮን አገልግሎት ሙከራ በተሳካ ሁኔታ እያደረገ ይገኛል።
ድሮኗ በዋናነት ክትባቶችን የምታጓጉዝ ሲሆን ከ15 ደቂቃ ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ በተፈለገው ስፍራ አድርሳ ትመለሳለች። በቀጣይ ከፍተኛ ክብደት ያለው በርካታ ክትባቶችን የሚያደርስ ድሮን ለማቅረብም በዝግጅት ላይ ይገኛል።
ለዚህ ትልቅ ተግባር የሚተጉ የድርጅት መስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊዎችና የሐዋሳ ከተማ መድኃኒት አቅርቦትና አገልግሎት ዋና ኃላፊ የሆኑት አቶ ዘመን ለገሰ ሊመሰገኑ ይገባል።
Via: ኤፍሬም




1 comment
ኢትዮጵያ ግን ቅብጥጥጥ አለች 😭😁