በሀገራችን ብቸኛ እና የመጀመሪያ የሆነውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የተማሪዎች ሽልማት ዓመታዊ ፕሮግራም ታህሳስ/2017 ዓ.ም በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም እንደሚካሄድ በዛሬው ዕለት ዝግጅቱን በተመለከተ ለሚዲያ አካላት በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።
የዚህ ሽልማት ትልቁ ዓላማ ውጤታማ ተማሪዎችን እና ምስጉን መምህራንን መሸለም፤ በመማር ማስተማሩ ምሳሌ የሆኑ የመንግስትና የግል የትምህርት ተቋማትን እውቅና መስጠት ሲሆን ለሀገራችን የትምህርት ልማት ሁለንተናዊ ለውጥ አስተዋጽኦ በማድረግ ለትውልድ ዓርዓያ መሆን የቻሉ ተቋማት፣ ድርጅቶችና ግለሰቦችም እውቅና የሚያገኙበት ዝግጅት እንደሆነ ተጠቅሷል።
በዚህ ሽልማት ላይም እጩ የሚሆኑት ለዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት በሀገር አቀፍ የደረጃ ከፍተኛ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች፣ ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ ከፍተኛ ነጥብ ያመጣች ሴት ተማሪ እና አካል ጉፈዳተኛ ተማሪ፣ 100% ወደ ዩኒቨርሲቲ ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች፣ በኮሚቴው መለኪያ ያለፉ እና እንደዕየድሜያቸው በጀነሬሽን ሶስት ዩኒቨርሲቲዎች፣ ምርጥ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሶስት፣ ከአጠቃላይ ትምህርት ምስጉን መምህራን ሶስት፣ ባለተሰጦኦ ተማሪዎች፣ የፈጠራ ባለቤቶች ሶስት፣ በትምህርት ልማት የተሳተፉ አምስት ባለሃብቶች፣ በሀገራችን የትምህርት ዕድገት የላቀ ሚና ለተወጡ ሶስት አለምአቀፍ፣ የህይወት ዘመን ተሸላሚ በተለያዩ ዘርፎች እንዲህም ልዩ ተሸላሚ እንደሚኖር ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የተማሪዎች ሽልማት በአዋጅ የተቋቋመ በሀገራችን ብቸኛው እና የመጀመሪያው ብሔራዊ የሽልማት ድርጅት ነው።





1 comment
ትልቅ አሻጋሪ ሽልማት ነው