banner

የሶሪያ ህዝብ የነፃነት፣ የፍትህ፣ የእኩልነት ቀንዲል ታጋይ

የሶሪያ አምባገነን መንግስት ዛሬ ላይ እንዲህ ይገረሰስ ዘንድ የሶሪያ ህዝባዊ እንቅስቃሴውን ወይም አብዬቱን ከጀመሩትና ከአቀጣጠሉት ግንባር ቀደም አንቂዎች ወይም መሪዎች አንዱ ጀግናው ማዘን አል ሃማዳ ሲሆን የሶሪያ ህዝባዊ እንቢተኝነቱ ከተጀመረበት 2002 ዓ/ም መጨረሻ ጀምሮ በ1.4 ካሬ ሜትር ክፍል ውስጥ ከ12 ታጋይ ጓዶቹ ጋር በአየር ኃይል ደህንነት ማጎሪያ ሜዜ ታስሮ የቆየና አሰቃቂ ወሲባዊ ጥቃት : ዘግናኝ ድብደባ ያሳለፈ ሲሆን አብዛኛው የትግል ጓዶቹ በድብደባ ብዛትና በተላላፊ በሽታ የሞቱ ሲሆን ታጋይ ማዘንም በፀና በመታመሙ ወደ ወታደራዊ ሆስፒታል 601 ተብሎ የሚጠራው የተዛወረ ቢሆንም እዛም የጠበቀው ህክምና ማግኘት ሳይሆን የበለጠ ስቃይ መከራ ግርፋት እንግልት ነበር ።

ታጋይ ማዘን ከአንድ አመት ከመንፈቅ አሰቃቂ የእስራት ጊዜ በኃላ በመፈታቱ ለህይዎት ደህንነቱ ሶሪያ መቆየቱ ስላሰጋው ከሃገር በመውጣት ለስደት የተዳረገ ሲሆን እድልም ቀንቶት በህገወጥ መንገድ ተጓጉዞ ወደ አውሮፕላን ኔዘርላንድ የፓለቲካ ጥገኝነት ከአገኘ በኃላ ምቹ የተደላደለ ህይወትን ለመምራት ሳይሆን ለተነሳበት የህዝቡን ሰላም : ደህንነት : ነፃነት : ፍትህ : እኩልነት ዓላማ ግብ ማድረስ ነበርና ስለ በሽር አላሳድ አምባገነን ስርዓት ድምጹን ከፍ አድርጎ ያለመታከት በማሰማትና ለተለያዩ ሃገራት እንደ አሜሪካ ባሉት በመጓዝ በህዝብ እንደራሴዎች ፊት እና በአለም አቀፍ ሚዲያዎች ላይ እየቀረበ የሶሪያን ህዝብ ሰቆቃ አንድ ራሱ ጉልህ ምሳሌ ሁኖ እያቀረበ ለማሳወቅ ችሏል ።

ታጋይ ማዘን የሶርያን ህዝብ ሰቆቃ በውጭ ሁኖ የቻለውን ያክል ድምጹ ሁኖ ሲታገል ቆይቶ በየማጎሪያ ቤቱ ያለውን ሰቆቃ ስለሚያውቀውና የአዕምሮ እረፍት ስለነሳው ህመም ስለሆነበት ወደ ሃገር ቤት ተመልሶ ለመታገልና ለማታገል ወስኖ በ2013 ዓ/ም ወደ ሶሪያ በተመለሰበት እለት የሰው ልጅ ማረ.ጃ ቄራ ተብሎ ወደሚጠራው የምድር ሲኦል ሲድናያ ተወረወረ : ታጋይ ማዘን በዚህ ቄራ ሲድናያ ከተወረወረበት እለት አንስቶ ለአለፊት አራት አመታት አስከሬኑ በሆስፒታል ፍሪጅ ውስጥ ከቀናት በፊት እስከሚገኝ ድረስ የትኛውም የትግል አጋሩ : እናት እህቶች ቤተሰብ ወዳጆቹ ለማየትም ለመጠየቅም አልቻሉም።

ታጋይ ማዘን አል ሃማዳ የሶሪያ ነፃ አውጭ ግንባር ኃይል በቀናት ውስጥ አምባገነኑን የበሽር አላሳድ መንግስት ከመገርሰሳቸውና የሰው ልጅ ማረጃው ቄራ ሲድናያ ከመቆጣጠራቸው ትንሽ ሰዓታት በፊት ያቀጣጠለውን ያስጀመረውን የሶሪያ የነፃነት ህዝባዊ እንቅስቃሴ የነፃነት የፍትህ የእኩልነት ብርሃን ሳያይ በአሰቃቂ መልኩ አካሉን ለመለየት በሚያዳግት መልኩ ተደብድቦ ተገድሎ ከበርካታ በግፍ ከተገደሉ ታጋዬች አስከሬን ጋር አስከሬኑ በሆስፒታል ማቀዝቀዥ ውስጥ ተገንቷል።

ታጋይ ማዘን አል ሃማዳ ለሶሪያ ህዝብ የእውነት የነፃነት የፍትህ የእኩልነት ትግል አስጀምሮና ዳር አድርሶ በመጨረሻዋ ሰዓት የህይወት መስዋዕትነት ቢከፍልም ታጋይ ማዘን በለኮሰው የነፃነት ትግል ችቦ የሶሪያ ህዝብ የ50 አመታትን ጨቋኝ ስርዓት ለመገርሰስ ችሏል። የታጋይ ማዘን አል ሃማዳ የትግል ህይዎትና አሳዛኝ አሟሟቱ እጣ ፈንታ ሁኔታ ዛሬ በአለም አቀፍ ሚዲያዎች ትልቅ የዜና ሽፋን ያገኘ ነው ፣ የታጋይ ማዘን አል ሃማዳ ቤተሰቦቹ የትግል አጋሮቹ በተገኙበት በደማስቆ በዛሬው እለት ተፈጽሟል ፣ አላህ ጀነተል ፍርደውስ ይወፍቅህ 🙏

በNegash Qemant

Leave a Comment