banner

የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ቅዳሜ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው

የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ቅዳሜ ታኅሣስ 12 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የሀገሪቱ ዲፕሎማሲያዊ ምንጮች አስታውቀዋል።

ፕሬዝደንቱ በዋነኛነት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋራ በመኾን፣ በሀገራቸው መንግሥት የገንዘብ ድጋፍ የታደሰውንና አዲስ አበባ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመንግሥት ወይም ኢዮቤልዩ ቤተ መንግሥት መርቀው እንደሚከፍቱም ጠቅሰዋል።

የፈረንሳዩ መሪ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋራ የሁለትዮሽ ውይይት እንደሚያካሂዱም እነዚሁ ምንጮች አመልክተዋል ሲል የአሜሪካ ድምፅ ዘግበዋል።

8 comments

Lidu Kl December 19, 2024 - 8:52 am

ችግር የለውም ይጎብኙ 😟

Reply
Lij Amani December 19, 2024 - 8:53 am

ወንድም ኢማኑኤል

Reply
Ababo D Wahima AB December 19, 2024 - 8:56 am

ስንት ሰው ይዘው እንደሚመለሱም አጣርልን 🤣

Reply
Coc Tail December 19, 2024 - 8:57 am

እኔ ያልገባኝ የነ አዳነች ተዘጋጅተናል ያሏት ነገር 😁😁

Reply
Teddy Girma December 19, 2024 - 8:58 am

የለሁም ቅዳሜ ደሞ እንዴት ነው ማደርገው 🤔

Reply
Atrsaw Hailemeskel December 19, 2024 - 9:00 am

❝ እኔ በበኩሌ ሥራ ስላለብኝ መገኘት አልችልም። ❞
✍️ከሚታይ ፊርማ ጋር!

Reply
አማረ ሙንየ December 19, 2024 - 9:02 am

አብረው እንደሚወስዱኝ ተስፋ አለኝ

Reply
Murad Bonger December 19, 2024 - 9:04 am

ደሞ ቅዳሜ እንቀማምሳለን፣

እንዳናስቀይማቸው😁

Reply

Leave a Comment