0
#FastMereja | ቻፓ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂስ ከልደታ ካቶሊክ ካቴደራል ትምህርት ቤት በጋራ ለመስራት የሚያስችለዉን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
ዛሬ ታህሳስ 14/2017 ዓም በትምህርት ቤቱ በተካሄድ የመግባቢያ ስምምነት የልደታ ካቶሊክ ካቴደራል የትምህርት ቤት ማስፋፋያ ህንጻ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ ከሚገኙ ከቀድሞ የካቴድራል ተማሪዎች እና ቤተሰቦች በቻፓ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ አማካኝነት ገንዘብ ለመሠብሰብ አላማ ያለው መሆኑን የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አባ ተክሌ መኮንን ገልጸዋል።
ቻፓ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂስ መስራች እና ስራ አስኪያጅ አቶ ናኤል ኃ/ማርያም ባደረጉት ንግግር የልደታ ካቶሊክ ካቴደራል ትምህርት ቤት እየተገበረ ለሚገኘው ኘሮጀክት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ በገንዘብ እርዳታ ለሚሰጡ ግለሰቦች ምቹ ሁኔታን ማዘጋጀታቸውን ገልጿል።
ድጋፍ አድራጊዎችም ተከታዮቹን ቻፓ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂስ ሊንኮች በመጠቀም ድጋፍ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል
👉https://chapa.link/donation/view/DN-xSsQVPX31N6s
👉https://chapa.link/donation/view/DN-xSsQVPX31N6s




