የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊና አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በዓመት ሁለት ጊዜ በክልሉ ርዕሰ መዲና ሀዋሳ በደማቅ ሁኔታ ይከበራል ብለዋል።
በዚህ በዓል ላይ ለመታደም ከሀገር ውስጥና ከባህር ማዶ የሚመጡ ምዕመናንና እንግዶች የሀዋሳን ሰላማዊትና ለመሰል ሀይማኖታዊና ክብረ በዓላት ብሎም ለቱሪዝም ምቹ መሆኗን የሚጠቁም ነው ብለዋል።
ዛሬ የተከበረው የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል ያለ ምንም ኮሽታ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ባማረ መልኩ እንዲጠናቀቅ የፀጥታ ሀይሉ እና ምዕመኑ በጋራ በመሆን ያበረከተው ታላቅ ስራ ስለመሆኑም ነው የቢሮ ሀላፊው የገለፁት።
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መኩሪያ ማርሻዬ በበዓሉ ላይ በመገኘት መልዕክታቸውን በማስተላለፍ ለምዕመኑ እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።
ከንቲባው በመልዕክታቸው አባቶች የሰጡንን ታላቅ ሀገር በጋራ በመሆንን እና በመቻቻል ከዳር ለማድረስ ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል።
ውቧ ከተማችን ሀዋሳ ይህን በዓል በታላቅ ጉጉት ከምጠብቀው አንዱ ሀይማኖታዊ ክብረ በዓል ውስጥ ይጠቀሳል ሲሉም ነው የገለፁት።
ለዚህ የከተማዋ ፍላጎት ውስጥ አንዱ የሆነው ከተማችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ያለውን የሀይማኖታዊ ክብረ በዓላት አከባበርን ጨምሮ የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት ፍላጎትን አጉልተን የምናሳይበት ልዩ ቀን በመሆኑ ነው ሲሉም ተናግረዋል ከንቲባው።
በዚህም እንግዶቻችን ከተለያዩ አካባቢዎች እና ክፍላተ አለማት በመምጣት በዚህ ቀን በከተማችን በዓሉን በልዩ ድባብ እያከበሩት እንደሚገኝ ማሳያ ነው ብለዋል።
የበዓሉ ታዳሚያንም በዚህ ቀን በከተማችን ሲገኙ ከሚያገኙት መንፈሳዊ በረከት ባሻገር ስለ ከተማችን አምባሳደር በመሆን ጭምር የበኩላቸውን እንዲወጡ የበኩላችንን ጥረት አድርገናል።
በዚህም ስኬታማ የሆነች ውብ ከተማን መገንባት ችለናል ብለዋል።
ለዚህ ደግሞ ሁላችንም የከተማዋ ከንቲባ ነን በሚል መንፈስና ታላቅ ተጋድሎ የበኩላችንን እንድንወጣ ይገባል ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የቅዱስ ገብርኤል የታህሳስ የንግስ በዓል በሀዋሳ ያለ ምንም የፀጥታ ስጋት ምዕመኑ መንፈሳዊ በረከቱን በመቀበል በዛሬው እለት በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል።
0





2 comments
ታቦት አጠግብ ምዕመን (ካህን ያልሆን ) መቀመጡ ከስርዓ ዉጭ ነዉ።
🥰🥰🥰🥰