banner

አሚጎስ የቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር በ2016 በጀት ዓመት ከ145 ሚሊዮን ብር በላይ አተረፈ

አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር የኅብረት ሥራ ማኅበር 11ኛ የባለአክሲዮኖች ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገበት ወቅት በ2016 በጀት ዓመት ከ145 ሚሊዮን ብር በላይ ማትረፉን ገልጿል።

አሚጎስ በበጀት አመቱ ያገኘው የተጣራ ትርፍም 101 ሚሊዮን ብር እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ካገኘው ትርፍ ላይ 30 በመቶ የሚሆነውን ለኅብረት ስራ ማኅበሩ መጠባበቂያ እንደሚያውለው አስታውቋል። ሰባ በመቶ የሚሆነውን ደግሞ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ለአባላቱ ባላቸው የአክሲዮን መጠን የትርፍ ክፍፍል ያደርጋል ተብሏል። ይህም 53 ነጥብ 19 በመቶ ሲሆን፥ በ2015 ዓ.ም ከነበረው 52 በመቶ አንጻር ብልጫ ያለው ነው ተብሏል።

የዛሬ 12 ዓመት አካባቢ በ20 መስራች አባላት የተመሰረተው አሚጎስ፥ አሁን ላይ ከስምንት ሺህ በላይ አባላት እንዳሉትና ከ2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ሀብት ስለማፍራቱ ተገልጿል።
አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር የኅብረት ሥራ ማኅበር በአሁኑ ጊዜ ከ 10,000 በላይ አባላት ሲኖሩት ከ 4 ሺ በለይ ለሚሆኑ የማህበሩ አባላት ከ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር በመስጠት ለአባላት የግል ስራ እንዲጀምሩ ፣ የቤት ባለቤት እንዲሆኑ፣ የስራ መኪና እንዲገዙ እንዲሁም በተለያየ የስራ ዘርፍ እንዲሰማሩና ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች ሰዎች የስራ ዕድል እንዲፈጥሩ በማስቻል ለሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገት ከፍተኛ አስተዋፃኦ በማድረግ ላይ ይገኛል።




Leave a Comment