👉በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በአምባሰል ወረዳ የሚገኘው የባዚ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን እርዳታ ይፈልጋል
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በአምባሰል ወረዳ የባዚ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በ1587 ዓ.ም የተመሠረተ ጥንታዊ ቤተ ክርስቲያን ሲሆን ከግሸን ደብረ ከርቤ ቅ/ማርያም ገዳም በምሥራቅ አቅጣጫ 20 ኪሎ ሜትር ላይ ወይም በደልባ አምሣለ ገነት ቅ/ጊዮርጊስ በታች ከቆላው ላይ ይገኛል፡፡
ይህ ቤተ ክርስቲያን በ1953 ዓ ም በእንጨትና በቆርቆሮ የተሠራ ሲሆን በዘመን ብዛት ስላረጄና ወለሉም ስለተሰነጣጠቀ በአዲስ መልክ በሕንጻ ለማሠራት ይቻል ዘንድ በአጥቢያዉና በአዲስ አበባ ኮሚቴ ተቋቁሞ እርዳታ በማሰባሰብና ችግሩን ለሰፊዉ ምዕመናን ለማድረስ በ 20/4/2017 ዓ.ም ፒያሣ ገነተ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ የገቢ ማሰባሰቢያ መረሀግብር ያዘጋጀ ቢሆንም የተጠሩ ሰዎች በአብዛኛው ባለመገኘታቸው የታሰበውን ገቢ ከማግኘት ይልቅ ለሌላ ወጪ መዳረጋቸውን ገልፀዋል።
ለዚህም ለመስራት የታሰበው ዋናዉን ቤተክርስቲያን ለማሰራት፣ቤተልሔሙን ለማሰራት፣እቃ ቤቱን ለማሰራት፣አዳራሽ ለማሰራት እና ለካህናት መተዳደሪያ ማዘጋጀት የታሰበ ሲሆን ለዚህም ወጪ በጠቅላላ አሁን ባለው የገቢያ ሁኔታ 7,801,860 (ሰባት ሚሊዮን ስምንት መቶ አንድ ሺ ስምንት መቶ ስልሳ ብር) እንደሚያስፈልግ የተገመተ ሲሆን ለዚህ ለተቀደሰ ዓላማ በመሽቀዳደም ከፃዲቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ፀጋና በረከት እናገኝ ዘንድ ጥሪ ቀርቧል።
ስለዚህ አቅማችሁ የፈቀደውን ያህል እንድትረዱ በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስምና በፃዲቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ስም እየጠየቅን የባንክ አካውንታችን የባዚ ተክለ ሃይማኖት ቤተ-ክርስቲያን ሂሳብ ቁጥር 1000502246287 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ መሆኑን በታላቅ ትህትና እንገልጻለን፡፡
ስልክ ቁጥር ፡- 0911551512
0913400914
0913586114
0925317689





1 comment
ትንሸ ልመናውን ጋብ አርጋቹ ነበር ጀመራቹ ደሞ