banner

በሬክተር ስኬል 5.8 የደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ዛሬ ለሊት ተከሰተ

በኢትዮጵያ በሬክተር ስኬል 5.8 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ፤ ከለሊቱ 9:52 መድረሱን የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መስሪያ ቤት አስታወቀ። ሰሞኑን ሲከሰቱ ከነበሩት የመሬት መንቀጥቀጦች ዘለግ ላሉ ሰከንዶች የቆየው ርዕደ መሬት፤ ንዝረቱ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች ተሰምቷል።

የለሊቱ የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተው በአፋር ክልል መሆኑን የአውሮፓ ሜዲትራንያን ሴይስሞሎጂ ማዕከል (EMSC) ተቋም መረጃ ያሳያል። ርዕደ መሬቱ የተከሰተበት ቦታ ከአቦምሳ ከተማ 56 ኪሎ ሜትር እንዲሁም ከአዳማ ከተማ 146 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ መሆኑን የአሜሪካ እና የአውሮፓ ተቋማት ገልጸዋል።

የአውሮፓው የምርምር ማዕከል የለሊቱን የመሬት መንቀጥቀጥ የልኬት መጠን 5.6 እንደሆነ በመጀመሪያ ገልጾ የነበረ ቢሆንም ከቆይታ በኋላ ወደ 5.8 ከፍ አድርጎታል። የመሬት መንቀጥቀጡ መጠን ከሰሞኑ ከደረሱት ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።

ከዚህ ክስተት ስምንት ሰዓት አስቀድሞ በሬክተር ስኬል 5.5 የደረሰ ርዕደ መሬት ተከስቶ ነበር። አርብ አመሻሽ 11 ሰዓት ተኩል ገደማ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥም እንደዚሁ በሬክተር ስኬል ልኬት አምስትን የተሻገረ ነበር። በዚህ ጊዜ የተመዘገበው የርዕደ መሬት መጠን 5.2 ነው።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

8 comments

Firaol Chimdesa January 4, 2025 - 3:58 am

ኢየሱስ ይመጣል ሊወስደን ይመጣል።
በርሱ ያላመኑ ከዚህ የባሰ ነገር ይጠብቃቸዋል።

Reply
Azar Ed Mn January 4, 2025 - 3:59 am

የኮዬ ፈጫ ኮንዶሚኒየም ህንፃዎችን አመሰግኑልኝ።በዚ ልክ የጎጃም ጭፈራ ጨፍረው አለመውደቃቸው ይገርማል።ከ3 አመት በኋላ ይወድቃሉ የተባለው ለካ ውሸት ነው🤔

Reply
Jaji Singl Man January 4, 2025 - 3:59 am

እጃቹን ወደፈጣሪያቹ ዘርጉካልሆነ ዘንድሮ ከባድ ነው

Reply
Birhan Getachew January 4, 2025 - 3:59 am

ኮዬ ለሊት9:51 ተሰምቶኛል ገጭ ገጭ የሚል
ነበር

Reply
ህይወቴ ነሽ ድንግል January 4, 2025 - 4:00 am

ዝናብ የሚያዘንበው መንግስታችን መሬት እንዳይንቀጠቀጥ ማድረግ አይሳነውም

Reply
Beti Fantaye January 4, 2025 - 4:00 am

5. ምናምን ግን ሌላ ሃገር ህንጻ ይገለብጣል አ

Reply
Gete Chakebo January 4, 2025 - 4:01 am

ሰለ ሀገራችን ኢትዮጵያ ሁለቸንም በየሀይማኖታችን እንፀልይ ፈጠራ ይታራቅልን🥺
ሀገራችን በደም ተጨማልቀሌቸ 💔💔

Reply
Abdul Hamid January 4, 2025 - 4:04 am

አዘጋገባቹ የደስታም ጭምር ይመስላል

Reply

Leave a Comment