0 እድሳቱ ሁለት ዓመታትን የፈጀው የታሪካዊዉ የመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ህንጻ ቤተክርስቲያን እድሳት ተጠናቆ ዛሬ ተመርቋል ፡፡ ህንፃ ቤተ ክርስቲያኑን መርቀው የከፈቱት ብፁእ ወ ቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትሪያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ ወ እጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሀይማኖት ናቸው። መንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን 81 አመታትን ያስቆጠረ ባለ ታሪክ ቤተክርስቲያን ነው።