0
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በ ምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት በቫንኩቨር ኆኅተ ሰማይ ቅድስት ማርያም ወቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አዘጋጅነት የጥምቀት በአል ለመጀመሪያ ጊዜ ትውፊቱን እና ሃይማኖታዊ ስነ ስርአቱን ጠብቆ በጥምቀተ ባህር በተዘጋጀ ቦታ ላይ በከተማው ባሉ አብያተክርስቲያናት በጋራ በታላቅ ድምቀት ይከበራል። በዚህ ታላቅ በአል ላይ እንዲገኙ ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።
በበአሉም ታቦታቱ በሊቃውንተ ቤተከርስቲያን፣ የሰንበት ት/ቤት መዘምራንና ምእመናን ታጅበው ከየአድባራቱ ወደ ጥምቀተ ባህር ይወርዳሉ። ከምሽት ጀምሮ ሌሊቱን የዝማሬ፣ ትምህርተ ወንጌል፣ ሥርዓተ ማኅሌት እና ሥርዓተ ቅዳሴ እንዲሁም የጸበል ርጭት ይከናወናል። እንዳያመልጣችሁ። በዚህ ታሪካዊ በአል ላይ ከመላው ቤተሰብዎ ጋር በመካፈል በረከትን ያግኙ ለልጆቾም ባህልዎንናን ትውፊትዎን ያሳውቁ።
ቅዳሜ ጥር 10 january 18
እሁድ ጥር 11 January 19,2025
Vancouver BC Canada
Address Riverside Banquet Halls 1231 Burdette, Street Richmond BC
አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት (ኤፌ 4÷5)