0
ጥር 10 ቀን 2017 ዓ.ም ቅዳሜ ምሽት ላይ 35 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ከየመናዊ ካፒቴን እና ረዳት ካፒቴን ጋር የያዘች ጀልባ ከጂቡቲ ተነስታ በባኒ አል-ሃካም ከተማ አል-ሃጃጃህ አቅራቢያ መስጠሟን በየመን የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አስታውቋል።
በአደጋው የዘጠኝ ሴቶች እና የአስራ አንድ ወንዶች ህይወት በድምሩ የ20 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ህይወት አልፏል። ከአደጋው የቀሩት 15 ኢትዮጵያውያን እና ሁለት የየመን የበረራ ሰራተኞች መትረፍ ችለዋል።
አክሎም ህገ-ወጥ ስደትን ለመከላከል በርካታ ጥረቶች ቢደረጉም፣ እ.ኤ.አ. በ2024 ብቻ ከ60,000 በላይ መደበኛ ያልሆኑ ስደተኞች ወደ የመን መድረሳቸውን ድርጅቱ ዘግቧል።
1 comment
ሀገሬ እስከመቼ በስደት ትሰቃያለሽ😭😭😭
😭😭😭😭😭