banner

በአማራ ክልል የኤች አይቪ ኤድስ ስርጭት መባባስ

የኤችአይቪ ኤድስ ስርጭት በሀገር አቀፍ ደረጃ መቀነስ ቢታይበትም በአማራ ክልል ግን አሁንም ወረርሽኝ በሚባል መልኩ እየተሰራጨ እንደሆነ ይነገራል የጤና ሚንስቴር ባወጣዉ መረጃም 605 ሺህ ሰዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ በቫይረሱ መያዛቸዉን ሲጠቁም በየዓመቱም ቁጥራቸው 7ሺህ 428 የሚደርስ ሰዎች በቫይረሱ ይያዛሉ 10,065 የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በበሽታው ምክንያት ይሞታሉ ይላል የአገራዊ የኤች አይቪ ስርጭት ግምት መረጃ።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የኤችአይቪ የስርጭት ምጣኔዉ 0.9 በመቶ ቢሆንም በአማራ ክልል ግን 1.2 በመቶ ነዉ ይላሉ አቶ ዉድነህ ገረመዉ በአማራ ክልል ጤና ቢሮ የኤች አይቪ ዘርፈ ብዙ ምላሽ ዳይሮክተሬት ዳይሬክተር።

«እኛ ጋር አሁንም ወረርሽኝ ላይ ነዉ ያለዉ ጥናቶቹ ከዚህ ቀደም 1.7 ነበር 1.6 ወረደ 1.28 ነበረ አሁን ደግሞ 1.09 ነዉ የሚባለዉ ስርጭቱ ነገር ግን ነባራዊ ሁኔታዉ አሁን ያለዉ በተለያዮ ግጭቶች ጋር ተያይዞ በተለይ ከክልል ክልል መፈናቀል ጋር ተያይዞ ወደ 41 የተፈናቃዮች መኖሪያ አሉ በዚህ በኩል ደግሞ የፀጥታ ችግሩ አለ የፀጥታ ችግሩ ደግሞ መፈናቀሎችና አስገድዶ መደፈሮች አሉ ከዚህ ጋር ተያይዞ የስርጭት ሁኔታዉ አስጊ ሁኔታ ላይ መኖሩን የሚያመላክቱ መረጃዎች ደግሞ አሉ»

በኤችአይቪ ላይ መዘናጋት መጨመሩን የሚናገሩት በአማራ ክልል በደማቸዉ ዉስጥ ኤችአይቪ ቫይረስ ያለባቸዉ ወጣቶች ማህበራት ጥምረት የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ብርሃነ መስቀል ሲሳይ ወጣቶች በከፍተኛ ደረጃ በክልሉ በቫይረሱ እየተያዙ ነዉ ይላሉ።
via: ዶይቼ ቬለ

Leave a Comment