0
#FastMereja I ፓስቶራሊስት ኮንሰርን የተመሰረተበትን 30ኛ አመት እና የኢትዮጵያ አርብቶ አደሮች የክብር እና የእውቅና መርሃ ግብር ዛሬ ጥር 17/2017 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል ተካሂዷል።
ፓስቶራሊስት ኮንሰርን የአርብቶአደር ማህበረሰቦችን ኑሮ ለማሻሻል በቁርጠኝነት እየሰራ ሲሆን ለአርብቶ አደር መብቶች እውቅና መስጠትን ከማበረታታት ጀምሮ በጤና፣ በትምህርት፣ በምግብ ዋስትና እና በሌሎችም ጠቃሚ ፕሮግራሞችን እስከ መተግበር ድረስ ብዙ ስኬቶችን እንዳሳኩ ተገልጿል።
ፓስቶራሊስት ኮንሰርን ራዕይው የኢትዮጵያ አርብቶ አደር ማህበረሰቦችን የተሻሻለ እና ዘላቂነት ያለው ኑሮ ሲኖሩ ማየት እና ከጎረቤት ሀገራት አርብቶ አደር ማህበረሰቦች ጋር ጠንካራ ትበብር መፍጠር ነው።
ፓስቶራሊስት ኮንሰርን የመጀመሪያው የኢትዮጵያ አርብቶአደሮች ቀን በዓል ጥር 17 (ጃንዋሪ 25) ቀን 1991 ዓ.ም በሶማሌ ክልል ሊበን ዞን በፊልቱ ወረዳ ፈልቱ ከተማ ላይ የተለያዩ አርብቶአደር ማኅበረሰቦች ተወካዮች የጎሳ መሪዎችና የወረዳው ነዋሪዎች በሰፊው በተሳተፉበት በድምቀት ማክበረ ጀመረ።





1 comment
ሸራተን ነው ሰመራ መከበር የነበረበት