banner

ለታራሚዎች የመፃህፍት ድጋፍ ተደረገ

“የንባብ ባህል ለትምህርት ጥራት” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ የታራሚዎች የንባብ ቀን ዓውደ ውይይት እና የመፃህፍት ድጋፍ በወራቤ ከተማ ማረሚያ ቤት በዛሬው ዕለት ተከናውኗል።

ይህ መረኃ ግብር በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ከስልጤ ዞን አስተዳደር፤ ከወራቤ ዩኒቨርሲቲ፣ከወራቤ ከተማ አስተዳደር፤ከስልጤ ዞን ባሕልና ቱሪዝም መምሪያ እና ትምህርት መምሪያ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን በዝግጅቱም የታራሚ ክፍሎች ጉብኝት፣ የላይብረሪ ምርቃት እና የተለያዩ በደራሲያን እና በምሁራን የንባብ ጥቅምን በተመለከተ ንግግርና ምክራቸውን ለታራሚዎች አስተላልፈዋል።

ንባብ ለሕይወት የሚበጅ በየትኛውም ስፍራ ሆነን ልንከውነው የሚገባ ጉዳይ ነው ያሉት የወራቤ ማረሚያ ቤት ሀላፊ ኮማንደር አወል ሁሴን ንባብ ለትምህርት ጥራት ብቻም ሳይሆን ለሀገር እድገትም ቁልፍ ነው ብለዋል። ኮማንደር አወል አያያይዘውም ታራሚዎች ምግብና ህክምና ብቻ እየሰጡ ማረም ብቻውን ታራሚውን መለወጥ አይቻልም ብለዋል።

ከተማሪዎች ባላነሰ ታራሚዎችም መፀሀፍ ያስፈልጋቸዋል ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ሀላፊ አቶ አባተ ካሳው ሲሆኑ አገልግሎቱ በመፀሀፍ እንታረም የሚል አባባል በመያዝ ሀገራችን ባሉ ሁሉም ማረሚያ ቤቶች በመዟዟር በመፅሀፍ ትምህርት ቤቶችን እንደሚደግፉት ሁሉ ማረሚያ ቤቶችንም እየደገፉ እንደሆነ ገልፀዋል።





Leave a Comment