በትፈረኮት አክሲዮን ማህበር በስልጥኛ ቋንቋ የሚሰራ ቴሌቪዥን ጣቢያ ለመክፈት የተቋቋማ ማህበር ሲሆን ። ይፋዊ የምስረታ ጉባኤውን በወራቤ የስልጤ ባህል አዳራሽ አካሂዷል ።
በምስረታ ጉባኤው የአክሲዮን ማህበሩ አባላት የሀገር ሽማግሌዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።
የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአክሲዮን ማህበሩ ስራ አስኪያጅ እንጅነር ሻፊ የሱፍ አክሲዮን ማህበሩ የስልጤ ህዝብን ባህል ታሪክ ለማሳደግ የማህበረሰብን ኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን ለማሳለጥ የሚስችል ቴሌቪዥን ለመክፈት አልሞ የተቋቋመ ማህበር መሆኑን ገልፀዋል ።
አክለውም በስልጤ ማህበረሰብ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ቴሌቪዥን ባለመኖሩ የማህበረሰቡን ባህል ታሪክ እና ቋንቋ ለማሳደግ ከፍተኛ ተግዳሮት መሆኑን ገልፀዋል በመላው አለም የሚገኘው የስልጤ ብሄር ተወላጅ በዚህ ድርጅ አክሲዮን በመግዛት እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል ።
የማህበሩ መስራች የሆኑት ጋዜጠኛ መሀመድ ስራጅ ተቋሙ ለማህበረሰብ እጅግ አስፈለጊ የሆነውን ቴሌቪዥን ጣቢያው መክፈት አላማው በመሆኑ የብሄሩ ተወላጆች በነቂስ ተሳታፊ መሆን እንዳለባቸው መልእክት አስተላልፈዋል ።
ጋዜጠኛ መሀመድ ሚዲያ በአሁኑ ወቅት ለማህቀረሰብ እንደ ኦክስጂን አስፈላጊ በመሆኑ ማህበሩን በመቀላቀል መስራት ለነገ የሚባል ጉዳይ አይደለም ብለዋል ።
በወራቤ ዩንቨርስቲ የጋዜጠኝነት እና ስነ ተግባቦት መምሩ አቶ ሳዲቅ ሽፋ በመድረኩ ጥናታዊ ፁሁፍ አቅርበዋል ። በጥናታዊ ፁሁፉ የስልጤ ህዝብ በአንድነት ተቀናጅቶ ከሰራ ቴሌቪዥን ማቋቋም የሚያስችል አስቻይ ሁኔታ እንዳለ አስረድተዋል ። የስልጤ ህዝብ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ያለመንግስት በጀት በመስራት የሚታወቅ ልማታዊ ህዝብ መሆኑ እንደ መልካም አጋጣሚ ሊወሰድ የሚችል አስቻይ ሁኔታ መሆኑን አብራርተዋል ።





1 comment
ሻፊ የሱፍ ጀግና።