banner

ከ50 ሺህ በላይ የሚሆኑ የትራፊክ ደንብ የተላለፉ ዜጎች እንደተቀጡ ባለስልጣኑ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን በ6 ወራት ዉስጥ ከ50ሺህ በላይ የትራፊክ ደንብ ተላልፈዉ የተገኙ ዜጎችን መቅጣቱን አስታዉቋል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በ6 ወራት ጊዜ ዉስጥ መንገዶችን ለእግረኛ ምቹ ማድረጉን እና ከ5መቶ በላይ የተማሪ ትራፊክ ፖሊሶችን ማሰልጠኑንም ገልጿል፡፡

ከ50ሺህ በላይ የትራፊክ ደንብ የተላለፉ ዜጎችን መቅጣቱን እና የተሽከርካሪ ማቆሚያ ቦታዎችን መገንባቱን የገለጹት በባለሥልጣኑ የአገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክተር አቶ ጎይቶም አስፋው ናቸዉ፡፡

ከደንብ ማስከበር ቢሮ ጋር በመሆን 1መቶ19 ሕንፃዎች ላይ አስተዳደራዊ ርምጃዎችን በመውሰድ የገንዘብ ቅጣት እንዲጣል መደረጉም ተገልጿል ሲል ኢትዮ ኤፍ ኤም ነው የዘገበው።

Leave a Comment