banner

አሜሪካ ለሚኖሩ (ተጨማሪ) መረጃ፡ የእጮኛ ቪዛና የስደተኞች አፈሳና መመለስ

🚨🚨
በጋዜጠኛ አበበ ፈለቀ

ትላንት ያጋራሁትን መረጃ ተከትሎ የእጮኛ (K-1 Fiancé(e) Visa ) ቪዛ ጋ ተያይዞ በውስጥ መስመር ተጨማሪ መረጃን የጠየቁኝ የተጨነቁ ኢትዮጵያውያን አሉ። ለነሱ የሰጠሁት መልስ ለሌሎችም ስለሚጠቅም እነሆ።

የእጮኛ ቪዛ አሜሪካ መጥታችሁ በ90 ቀን ውስጥ ጋብቻ እንድትፈጽሙ የሚያስገድድ ነው። በ90 ቀን ውስጥ ተፈራርማችሁ የስራ ፍቃድ (Work Permit) እና የመኖርያ ፍቃድ (Green Card) ማመልከት ይኖርባችኋል።

በዚህም መሰረት የሚከተለው ነጥቦች መሰረታዊ ናቸው።

✅ በ90 ቀን ውስጥ ተፈራርማችሁ፣ ለመኖርያ ፈቃድ(Green Card) እና የስራ ፈቃድ (Work Permit) ካመለከታችሁ፣ እንዲሁም ምንም አይነት የወንጀል ታሪክ ከሌላችሁ ቪዛው ጊዜው ቢያልፍም የዚህ ዘመቻ ኢላማ አይደላችሁም።
✅ ጉዳዩ በሂደት ላይ ቢሆንና መኖርያ ፈቃዱና የስራ ፈቃዱ ባይመጣም እንኳን የማመልከቻችሁን (I-485 እና I-765) ደረሰኝ እና የጋብቻ ማስረጃችሁን ቅጂ ይዛችሁ መንቀሳቀስ ትችላላችሁ።
**********

🔴በ90 ቀናት ውስጥ ጋብቻውን ካልፈጸማችሁ፣ ጋብቻውን ፈጽማችሁም የመኖርያ ፈቃድ ወይም የስራ ፈቃድ ማስተካከያ ማመልከቻ ያላስገባችሁ፣ የወንጀል ክስ፣ መዝገብ ወይም ታሪክ ያላችሁ ወይም የቪዛው የጊዜ ገደብ ያለፈባችሁ የዚህ አዲስ ህግ ኢላማ ልትሆኑ ትችላላችሁ።
************

ትላንት በዝርዝር የቀረቡት መረጃወችም ከላይ ከተጠቀሱት በተለይ ከእጮኛ ቪዛ ጋ ከተያያዙት መረጃወች ጋ በጋራ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ። በድጋሚ ይሄ መረጃ እንደ ተጨማሪ መረጃ የሚጠቅም እንጂ ከጠበቆቻችሁ ጋ የምታደርጉትን በጉዳያችሁ ላይ ያተኮረ የምክር አገልግሎት የማይተካ መሆኑን አስታውሳለሁ።

#Ethiopia #Ethiopiandiaspora #immigration #USImmigration

1 comment

Mõĥãmmêď Ĩbňū Ŝēmmëř January 30, 2025 - 2:27 pm

በእውነት ጨንቆን ነበር ተባረክ።🙄😎

Reply

Leave a Comment