banner

ብናልፍ አንዱዓለም በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው በመሾም ቃለመሐላ ፈጸሙ

የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለም በአሜሪካ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው በመሾም ቃለመሐላ ፈጸሙ።

ባሳለፍነው ህዳር ወር ላይ የተሾሙት አምባሳደር ብናልፍ አንዱዓለም በዛሬው ዕለት ቃለመሐላ በመፈጸም ከፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የሹመት ደብዳቤ እና የሥራ መመሪያ ተቀብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ በወቅቱ አምባሳደሮች ህዝብና መንግሥት የማገልገል ኃላፊነታቸውን በታማኝነት እንዲወጡ አሳሰስበዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል።

አዲሱ ተሿሚ አምባሳደር ብናልፍ አንዱዓለም በጥበብ እና በብልሀት የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ ወዳጅነትን እንዲያስቀጥሉ አደራ ብለዋል ተብሏል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ለ120 ዓመታት የተሻገረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዳላቸው አስታውሰው፤ አምባሳደር ብናልፍ አንዱዓለም በዜጋ ዲፕሎማሲ፣ በኢኮኖሚ፣ በጸጥታ እና ደኅንነት የኢትዮጵያን ጥቅም የማስጠበቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

Leave a Comment