አዲስ ጃዝ ፌስቲቫል ከጥር 30 እስከ የካቲት 2 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በመሃል አዲስ አበባ በሚገኘው የስዊድን ኤምባሲ እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል
የዚህ ዓመቱ ዝግጅት የኢትዮ-ጃዝ አንጋፋ ትሩፋቶች የሚከብሩበት እንዲሁም የተለያዩ የሙዚቃ አይነቶች የሚንጸባረቁበት በዚህም የባህል ልውውጥ የሚካሄድበት እንደሆነ የሰላም ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሳሙኤል ሙሉጌታ ተናግረዋል::
በሙዚቃዊ እና ሰላም ኢትዮጵያ የተዘጋጀው ይህ ፌስቲቫል ድንቅ አገር በቀል እና ዓለም አቀፍ እርቲሰቶችን፣አውደ ጥናቶችን፣የፓናል ውይይቶችን እና ባህል-ነክ እንቅሰቃሴዎችን ይዟል።
የዘንድሮ አዲስ ጃዝ ፌስቲቫል ሙዚቃ፣ ሥነ-ሥዕል እና የአገር ውስጥ ባህላዊ የዕደ ጥበብ እና ቅርፃ ቅርፅ የመገበያያ ስፍራዎችን ለታዳሚዎች ያቀርባል።
በፌስቲቫሉ ኩኩ ሰብስቤ፣ ፍቅረአዲስ ነቃጥበብ እና የኢትዮጵያ እንጋፋ ሙዚቀኞች ዳዊት ይፍሩ እና ሮሃ ባንድ አለም አቀፍ ሙዚቀኞች ከሆኑት ሰቱዋርት ሱኩማ እና ንኩቫ ባንድ (ከሞዛምቢክ)፣ ማፔይ (ከሰዊድን) እና ዊንዮ (ከኬንያ) እንዲሁም በአዲስ አበባ በሚስተዋለው የጃዝ ትዕይንት ላይ የጃዝ ቁንጮዎች ከሆኑት መካከል ቃየን ላብ፥ ሳሙኤል ይርጋ፥ ሀዲንቆ እና በረከት አበበ በፌስቲቫሉ ላይ ስራቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን በተጨማሪም የዚህ አመቱ ፌስቲቫል ኢትዮ-ጃዝ እና ሂፕ ሆፕን በማዋሃድ በሰራው በአይነቱ ልዩ በሆነ ሙዚቃ የሚታወቀውን ጀምበሩን እንዲሁም የትግራይ ባህል ቡድንን እንደያዘ የአዲስ ጃዝ ፌስቲቫል የሙዚቃዊ ስራአኪያጅ አቶ ሲሳይ መንግስቴ ተናግረዋል።
ሙዚቃዊ እና ሰላም ኢትዮጵያ የኢትዮጵያን ደማቅ የባህል እና የሙዚቃ መልክዓምድር በመቅረጽ ረገድ እየሰሩ የሚገኙ ድርጅቶች ሲሆኑ ሙዚቃዊ የኢትዮጵያን የካበተ የሙዚቃ ቅርስ፣ትሩፋት ጠብቆ በማቆየት እና በማስተዋወቅ ላይ ትኩረት ያደረገ የሙዚቃ አሳታሚ እና የሁነት እዘጋጅ ፤ ሰላም ኢትዮጵያ ደግሞ የአርቲሰቶችን መብቶች ወደ ፊት ለማራመድ እና የኢትዮጵያን የፈጠራ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለማሳደግ እየሰራ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው፡፡


