banner

ቤንዝል አንድ ሊትር 500 ብር እየሸጡ የነበሩ ግለሰቦች በአርባምንጭ ከተማ በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ህዝቡን እያስለቀሱ ሲኖሩ የነበሩ ደላሎች እና ባለስልጣናት በአርባምንጭ ከተማ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ።

በአርባምንጭ ከተማ ቤንዚል በመደበቅና በህገወጥ ንግድ ስራ የተሰማሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአርባምንጭ ፖሊስ አስታወቀ።

እነዚህ ደላሎች ከጥቂት የዞኑን እና የከተማ አመራር ጋር በመመሳጠር በህዝብ ዕንባ ላይ ሀብት ሲያካብቱ የነበሩ እንደሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን ደላሎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉ ቢሆንም ከእነዚህ ቡድኖች ጋር ሲተባበሩ የነበሩ ባለስልጣናትን በተመለከተ ምርመራ እየተካሄ እንደሆነ እና ባለስልጣናቱ ላይ ከህግ ተጠያቂነት በተጨማሪ ፖለቲካዊ እርምጃም ሊወሰድ መሆኑን ተገልፆል።

እነዚህ ደላሎች እና ባለስልጣናት በአርባምንጭ ከተማ ህዝቡ በቤንዚል እጥረት እየተሰቃየ 1 ሊትር ቤንዚል በኮንትሮባንድ ከ450-500 ብር እንዲሸጥ እያደረጉ እና በቀን እስከ 40,000 ሊትር በኮንትሮባንድ ሲሸጡ የተያዙ ናቸው ብሏል የአርባምንጭ ፖሊስ።

ከዚህም በተጨማሪ ከፍተኛ መጠን ባለው የኮንትሮባንድ ስራ ተሰማርተው እየሰሩ እንደነበርና በሰነድ ማጭበርበር ስር ይሰሩ እንደነበር ተገልፆል

የደቡብ ክልል መንግስት እና የብሔራዊ ደህንነት ተቋሙ በቅንጅት ይህን ኦፕሬሽን በመስራት ተጠርጣሪዎቹን እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር እንዳዋሉት ለማወቅ ተችሏል።

10 comments

Sisay Dem Sis February 9, 2025 - 6:24 pm

የዜናው ምንጭ ይጠቀስ

Reply
እዮብ መኮንን February 9, 2025 - 6:26 pm

የመንግስት ካድሬዎች ስራ እኮ ነው

Reply
Mekdes Shimekt February 9, 2025 - 6:26 pm

ነዳጅ ለመሆኑ አለ ወይ🤔

Reply
Tebarek Kersme February 9, 2025 - 6:26 pm

በስንት ገዝቶ

Reply
Zelalem Gizaw Bekele February 9, 2025 - 6:28 pm

This shows why African as a continent poor!

Reply
Tadesse Damesse February 9, 2025 - 6:28 pm

ይህ በደቡብ አከባብ የቆዬ የለብነት ሥራ ነው ደላላው ከባለስልጣናት ጋር ሆኖ ነዳጅ ከማዳያ ይቸበቸባል፡፡

Reply
Ñëbã Kolaso February 9, 2025 - 6:30 pm

በ 500 ከተገኘማ ምርጥ ነው😍

Reply
Mõĥãmmêď Ĩbňū Ŝēmmëř February 9, 2025 - 6:32 pm

ግልባጭ ለመላው እትዮጵያ ክልሎች እና ዞኖች😎

Reply
Melaku Lekenaw February 9, 2025 - 6:33 pm

Endet new mekina minedaw ?

Reply
Andu Ashämé February 9, 2025 - 6:34 pm

ኧረ ጅንካ አካባቢም 600ብር እየተሸጠ ነበር ሰሞኑን

Reply

Leave a Comment