banner

በአዲስ አበባ የነዳጅ አቅርቦት ችግር እና አሽከርካሪዎች ምሬት

መዲናዋ አዲስ አበባ ውስጥ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በየወራት መጨረሻ እና የመጀመሪያ ቀናት የሚከሰተው የነዳጅ እጥረት የተለመደ ጉዳይ ሆኖ እየተስተዋለ ነው፡፡

በየነዳጅ ማደያዎቹ የሚስተዋሉ የተሽከርካሪዎች ሰልፍ ነዳጅ ቀድቶ ወደ እንቅስቃሴ ለመግባት ሰዓታትን ይፈጃሉ፡፡

በየነዳጅ ማደያዎቹ ተሰለፉ በርካታ አሽከርካሪዎችም “አሁንማ የለመድነው ጉዳይ ሆኗል” ያሉት የነዳጅ ሰልፉ ከስራቸው ክፉኛ እንደሚስተጓጉላቸው ያስረዳሉ፡፡

አንዳንዶቹ ከስራ ሰዓታቸው የሚጠፋውን ጊዜ ለመታደግ ሲሉ ሰልፉ ይቀንሳል ብለው ባሰቡበት ወቅት በሌሊት ነዳጅ ለመቅዳት እንደሚሰለፉ ያስረዳሉ፡፡

ከሰሞኑ ምክንያቱ ባልታወቀ ጉዳይ በርካታ በተለይም በመሃል የከተማዋ ክፍሎች የሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ዝግ ሆነው መስተዋላቸው ለእጥረቱ መባባስ እንደ አንድ ምክንያት ተጠቅሷል፡፡

ከዚህ በፊት ነዳጅ በወቅቱ ወደ ማደያዎች ደርሶ ለተጠቃሚዎች እንዳይከፋፈል በማድረግ ማስተጓጎል ፈጥሯል ተባሉ የነዳጅ ማጓጓዛ ተሽከርካሪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃዎች መወሰዱን የንግድና ቀጣናዊ ሚኒስቴር አስታውቆ ነበር፡፡

“የእርምት” የተባሉ እርምጃዎቹ ግን ለችግሮቹ መፍትሄ ሲያመጡ አይታዩም። ይልቁኑ የነዳጅ እጥረቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ አሽከርካሪዎችንም እየፈተነ መሄዱ ነው የሚታየው፡፡

መንግስት በየጊዜው የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ተመን ሊያሻሽል ነው የሚለውን የሚጠባበቁ የነዳጅ አከፋፋይና ሻጮች “የአለአግባብ ትርፍ” ለማግኘት አገልግሎቱን አለማቀላጠፋቸው ግን ለችግሩ በምክንያትነት ሲጠቀስ ቆይቷል፡፡

የዶይቼ ቬለ ዘገባ ነው።

Leave a Comment