0
#FastMereja I #ዜና I የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ለፓርላሜንታዊ ዴሞክራሲ ዕድገት ላበረከቱት የጎላ አስተዋጽኦ ከሩስያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የክብር ኒሻን ተሸልመዋል።
ሽልማቱን ያበረከቱት የሩስያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ሊቀመንበር ሚስዝ ቫለንቲና ማትቪዬንኮ ናቸው።
የክብር ኒሻኑ በሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ቻምበር ሲወሰን ብቻ ለምክር ቤቶች ፓርላሜንታዊ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ለሩስያና ለውጭ አገራት ዜጎች እንደሚሰጥ ገልፀዋል።
ለዚህ የእውቅና ሽልማት በመብቃታቸውም አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገርን እንኳን ደስ ያለዎት ብለዋቸዋል።
አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በበኩላቸው፥ ለተሰጣቸው የእውቅና ሽልማት የሩስያ ፌዴሬሽን ምክር ቤትን በኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤትና በራሳቸው ስም አመስግነዋል።
የኒሻን ሽልማቱ ለፌዴሬሽን ፓርላሜንታዊ ዕድገት የበለጠ እንዲሠሩ የሚያበረታታቸው መሆኑንም ገለጸዋል።
Via: EBC

10 comments
ንጉስ በሀገሩ የማይከበርበት እዚህም ሸልሙልኝ 😭
ምን ይገርማል ኮሜድያኑም ኖቤል ተሸልሞ የለ እንዴ 😁
👍👍👍👍👍👍👍🇪🇹 ይገባቸዋል ክቡር ፕሬዚዳንት ለወለኔም ጉዳይ ያበረከቱት በታሪክ የሚረሳ አይደለም የተቆለፈውን ደባ
መክፈት ያለ ጥቅም በእውነት መንገድ !!!
ሽጉጡን እንድጠጣ ለማበረታት ይሁን የሸለሙት😁
ምን ይገርማል ኖቤልም ተሸልመን የለ እንዴ 😁
ወንድሙ ነው
አገኘሁ አላገኘሁ ምን አገባችሁ🙄🙄🙄
ሩሲያም እንደ ጎንደር ሆነች😭
መቼም በባዳነት መሆን አለበት
ተሸላለሙ