banner

ጦር ሀይሎች የተገነባው ግዙፉ ባቡረያን መስጅድ በይፋ ተመረቀ!

#FastMereja I በአዲስአበባ ከተማ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ጦር ሀይሎች የተገነባው ግዙፉ ባቡረያን መስጅድ በዛሬው ዕለት በድምቀት ተመርቋል።

በምርቃት ስነስርአቱ ላይ የፌዴራል እና የአዲስአበባ መጅሊስ አመራሮች ፣የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ መጅሊስ አመራሮች ፣ኡለማኦች ፣ባለሀብቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በአካባቢው ሙስሊም ማህበረሰብ እርብርብ ፣በአህለል ኸይር ወንድሞች እንዲሁም በሜድሮክ ኢንቨስትመንት አማካኝነት ተገነባው መሆኑ ተገልጿል።

መስጅዱ አጠቃላይ ስፋቱ ከ2000 ካሬ ሜትር የሚልቅ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የወንዶች መስገጃ ፣የሴቶች መስገጃ የመሰብሰቢያ አዳራሽን ጨምሮ አጠቃላይ ባለ ሶስት ወለል መስጂድ ነው።

በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዲስአበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕረዚዳንት ሼይኽ ሱልጣን አማን “ባቡረያን መስጅድ ለከተማችን ሌላ ውበት የሚያላብስ ለእኛም ኩራት የሚሆን መስጅድ ነው ያሉ ሲሆን በመስጅዱ ግንባታ አሻራቸውን ላሳረፉ ሁሉ አላህ በኸይር ይመንዳቸው” ሲሉ ተናግረዋል።

በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የፌዴራል መጅሊስ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም መስጅዱ የሚገኝበት የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የመጅሊስ የስራ ሀላፊዎች የመስጅዱን ምርቃት አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የመስጅዱ ምርቃት ፕሮግራም ላይ ለመስጅዱ ግንባታ አስተዋጽኦ ለነበራቸው ግለሰቦች እና ተቋማት የምስጋና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ዘገባው የሀሩን ሚዲያ ነው
#ማህበራዊ





Leave a Comment