0
#FastMereja I በማህበራዊ ጉዳይ የቪዛ ማማከር እና ሰነድ የማደራጀት ስራ እንሰራለን በማለት በአዲስ አበባ ቢሮ ከፍተው በርካታ ሰው ከመዘገቡ በኋላ የተቋቋሙበትን አላማ ወደ ጎን በመተዉ ወጣቶችን በመዝረፍ ላይ ይገኛሉ ሲል ተበዳዮች ለፋስት መረጃ ቅሬታቸውን ገልጿል።
🇨🇦 ካናዳ
🇷🇴 ሮማኒያ
🇷🇺 ሩሲያ
🇧🇾 ቤላሩስ
🇵🇱 ፖላንድ
ወ ዘ ተ ሀገራት እንልካለን በማለት በተለያየ ጊዜ ወጣቶችን በማታለል ከወጣቶቹ ብር በርካታ ገንዘብ እንደሰበሰቡ ነው የተገለፀው።
ተገልጋዩ አገልግሎቱን ሳያገኝ ሲቀር በውሉ መሰረት የከፈለዉ ገንዘብ ድርጅቱ እንዲመልስለት ይገልፃል ግን ገንዘብ ስንጠይቅ ድርጅቶቹ በወጣቱ ላይ ግርፊያ፣ ድብደባ እና የድርጅቱን ስም በመቀየር ይህንን የሚባል ደርጅት አላውቀዉም የሚል መልስ ይሰጣሉ ብለዋል።
በዚህ ጉዳይ ላይ በተለያየ ጊዜ ለመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ ለፀጥታ ሀይሎች፣ እንዲሁም ለብራንድ አምባሳደሮቹ አቤቱታ እያቀረብን ብንገኝም ገንዘቡ እስካሁን አልተመለሰልንም ብለዋል።
