0
#FastMereja I በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኮንትሮባንድ ንግድ በመስፋፋቱና የጥሬ ገንዘብ እጥረት በማጋጠሙ እጃቸው ላይ ገንዘብ ያላቸው አትርፈው መሸጥ ጀምረዋል ተባለ፡፡
እንደማሳያም 90,000 ብር በ100,000 ብር ይሸጣል፡፡
ከባንኮች አንድ ሰው በቀን ከ500 ብር በላይ ማውጣት አይችሉም ተባለ፡፡
የህዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት አባል እና የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ መብራቱ አለሙ የጥሬ ገንዘብ እጥረት በባንኮች መፈጠሩን እና የኮንትሮባንድ ንግድ መስፋፋትን የተመለከቱት በምርጫ አካባቢያቸው በመተከል ዞን በመገኘት ባደረጉት ህዝባዊ ውይይት መሆኑን ለሸገር ነግረዋል፡፡
የኑሮ ውድነቱ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ተባብሷል የሚሉት የህዝብ እንደራሴው ይህንንም በህዝባዊ ውይይታችን ተመልክተናል ብለዋል፡፡
ዘገባው የሸገር ሬዲዮ ነው።

10 comments
90 ሺ ብር የት አለ 🙄
ቤንሻንጉል መጣሁልሽ 🏃♂️🏃♂️🏃♂️
በመሀል አገር ያለው ሁሉን ያላማከለ ሥርዓት ወደነዚ አከባቢም ቢያንስ ጠጋ ብሎ ብያይ ምን አለበት?!
በቀን ከ500 ብር በላይ ምን ያደርጋል ትክክለኛ ውሳኔ ነው
Real
ምነው አንዲ ረከስ😌😌😌😌
ወይ ኢትዮጵያ
fast አሶሳ ነኝ የት አካባቢ ነው እንደዚህ የምትሸጠው ?በውስጥ ንገረኝ
100 ሺ transfer ተደርጎ 90 ሺ በካሽ🤔
ነገ ብሄድ መች ደርሳለሁ??