0
#FastMereja I ሜሪ ዲዳ ፕሮሞሽን እና ኤቨንት «ካሜቲ ፖድካስት» የተሰኘ ፕሮግራም አዘጋጅቶ በኦቢኤን ቴሌቪዥን ለማስተላለፍ ነው የመግባቢያ ስምምነቱ የተፈፀመው።
ካሜቲ ፖድካስት እያዝናና ቁምነገር የሚያስጨብጥ ታዋቂ ሰዎች ያለፉበትን ውጣ ውረድ ለማህበረሰቡ የሚያካፍሉበት ፕሮግራም እንደሆነ የሜሪ ዲዳ ፕሮሞሽን እና ኤቨንት ስራ አስኪያጅ ሜሪ ዲዳ ገልጻለች።
የኦቢኤን ቴሌቪዥን ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ፍሰሃ በላይነህ እያዝናና ቁምነገር የሚያስጨብጠው ካሜቲ ፖድካስት በአጭር ጊዜ ውስጥ በኦቢኤን ቴሌቪዥን እንደሚቀርብ ተናግሯል።




1 comment
Waan dansaa