banner

መንሽ የተሰኘ የዲጂታል የንግድ ሥራ ልማት አገልግሎት (Digital BDS) መስጫ መተግበሪያ ይፋ ተደረገ፡፡

#FastMereja I የንግድ ሥራ ልማት አገልግሎት (BDS) ዘመናዊና ተደራሽ ለማድረግ መንሽ የተሰኘው መተግበሪያ በተለይ ሥራ ጀማሪዎችን እና አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን በባለሙያ ምክር፤ ክፍተትን መሰረት ያደረገና ለውጥ የሚያመጣ ሥልጠና፣ ወቅታዊ የገበያ መረጃ እንዲሁም የመነሻና የስራ ማሳለጫ አነስተኛ ብድር አገልግሎቶችን ከተለያዩ የገንዘብ ተቋማት ጋር በትስስር በማቀናጀት ትርጉም ያለው ለውጥ የሚያመጠ የንግድ ሥራ ልማት አገልግሎትን አካታች በሆነ ተመጣጣኝ ክፍያ ማቅረብ ያስችላል ተብሏል፡፡

መተግበሪያው በዘርፉ ከተደረገ ጥናትና ምርምር በኋላ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች እና የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች መሠረታዊ ፈተናዎችን በመለየት፤ ወቅታዊና የገበያ አውዱን ያገናዘበ፣ የአገልግሎት ጥራት ማሻሻያ እንዲሁም በዘርፉ የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት ለመቀነስ ታሳቢ ያደረገ መፍተሄ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡

ዛሬ በአዲስ አበባ ማዶ ሆቴል በተካሄደው የመንሽ ዲጂታል የንግድ ሥራ ልማት አገልግሎት መተግበሪያ ማስተዋወቂያ ሥነ-ሥርዓት ላይ በርካታ የአገር ውስጥና የውጭ ድርጅቶች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

መንሽ መተግበሪያን ያበለጸገው ብሩሀ ማይንድስ ኮንሠልትን ወክለው መግለጫ የሰጡት አቶ መክብብ ዘሪሁን፤ መንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ የልማት አጋሮች – ለኢንተርፕራይዞች መቋቋምና ሥራ ፈጠራ ልዩ ትኩረት በመስጠት እንዲሰሩና፣ ከዚህ ቀደም በዘልማዳዊ መንገድ ጥራቱን ያልጠበቀ የንግድ ሥራ ልማት አገልግሎት በነጻ ወይም የለጋሾችን እርዳታ መስረት ያደረገ አገልግሎት መሰጠቱ ያስከተለውን የጠባቂነት ዝንባሌ በማስቀረት የገበያ ስርዓት መሰረት ያደረገ አገልግሎት እንዲቀርብ በቁርጠኝነት እንዲተባበሩ ምክረሃሳባቸውን ለግሰዋል።

ብሩህማይንድስ ኮንሠልት በጥናትና ምርምር፣ ስልጠናና ደረጃውን የጠበቀ የንግድ ሥራ ልማት አገልግሎቶቹ የሚታወቅ ሲሆን፣ መንሽ የተሰኘው መተግበሪያም የድርጅቱን አገልግሎት ለብዙሃን በቅናሽ ለማድረስ ያለመ እንደሆነ ገልጸው በዝግጅት ሂደቱ የተባበሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ባለድርሻ አጋሮችን ከልብ አመስገነዋል፡፡

መተግበሪያን ከጎጉል ፕለይ እና አፕሰቶር በማውረድ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት እጅግ ተመጣጣኝ በሆነ ክፍያ ማግኘት እንዲጀምሩ ባለሙያዉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡





Leave a Comment