#FastMereja I በሀገራችን ኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት ዘርፍ ለይ የአካል ጉዳተኝነቱ ሳይገድበው የራሱን የሆነ ጉልህ አሻራ ማሳረፍ የቻለ እና ለብዙዎች የይቻላል መንፈስን በተግባር ያሳየው ጋዜጠኛ ተስፋዬ ገ/ማርያም ዛሬ መጋቢት 13/2017 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ በተዘጋጀ መርሃ ግብር የአብሮነት ስልጠናና ማማከር ዎርኪንግ ፋሲሊቴቲንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር አመራሮች እና አባላት፣ የመንግስት አካላት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ሰዎች እና ሚዲያዎች በተገኙበት የመኪና ሸልማት ከአብሮነት ተበርክቶለታል።
ሽልማቱን የተቀበለው ጋዜጠኛ ተስፋዬ ገ/ማርያም “ሰው ባለው ላይ ማተኮር ከቻለ ድል ማድረግ ይችላል፣ ይህ ለ25 ሚሊዮን አካል ጉዳተኞች ድምፅ ስለሆንኩ ለእነሱ እንደተሰጠ ነው” ብሏል።
አብሮነት ስልጠናና ማማከር ዎርኪንግ ፋሲሊቴቲንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር ከ30,000 በላይ አባላትን በማፍራት በዲጂታል ዕቁብ ሲስተም እንዲጠቀሙ እያደርገ ያለ ሀገር በቀል ድርጅት ነው።
ብዙ ሰዎችን በማሰልጠን በስራ ዕድል ፈጠራ እንዲሁም የራሳቸውን ስራ እንዲሰሩ እና በዲጂታል እቁብ በመታገዝ መነሻ ካፒታል በማግኘት ህልሞቻቸውን እንዲኖሩ እያደረገ ያለ ተቋም መሆኑ በመድረኩ ላይ ተገልጿል።




