banner

2.3 ሚሊዮን ብር የወጣበት ገመሃልያ ፊልም ለዕይታ ሊቀርብ ነው

#FastMereja I በእውነተኛ ታሪክ ተመስርቶ የተሰራው የፍቅር ፊልም «ገመሃልያ» በኪማ ፊልምስ ተዘጋጅቶ በፀጋ መልቲሚዲያ ለእይታ ሊቀርብ ነው።

የፊልሙ ዳይሬክተር የባለክራር ፊልም ደራሲና ዳይሬክተር የሆነው ሳሙኤል (ባዩሽ) ሲሆን በድርሰት ኤፍሬም ሃግስ ተሳትፏል፣ 1 ሰዓት ከ50 ደቂቃ ርዝመት ያለው ፊልሙ በፀጋ መልቲ ሚዲያ (ፀጋ አባተ) ፕሮዲውስ ተደርጓል።

በትወና ሰለሞን ቦጋለ፣ አዜብ ወንድሰን፣ ድምፃዊያን ቃልኪዳን እና ሙላለም ታከለ ተሳትፈውበታል።

መጋቢት 15 ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ታዋቂ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች በተገኙበት በአለም ሲኒማ የሚመርቅ ሲሆን፡፡ እንዲሁም መጋቢት 19,20,21 እና መጋቢት 26,27,28 በሁሉም ሲኒማ ቤቶች ይመረቃል እንዲሁም በአሜሪካን ሀገር ይመረቃል።

ለቀረፃ 1 አመት ከ6 ወር የወሰደ ሲሆን፣ 2.3 ሚሊዮን ብር በላይ ወጥቶበታል።

«ገመሃልያ» ማለት ታግሎ በማሸነፊያው ሰዓት እጅ የሰጠ፣ሞትን የመረጠ ማለት ነው።





3 comments

Yosef Kinfe Asirat March 21, 2025 - 9:45 am

Kirubel Seyoum-Haben
ገመሀልያ ማለት ታግሎ በማሸነፊያው ሰዓት እጅ የሰጠ፣ ሞትን የመረጠ ማለት ነው።
ለቀባሪ ላርዳ ብዬ ነው።

Reply
Minte David March 21, 2025 - 9:45 am

Ere እዛው እዩት🙌

Reply
Koku Buta March 21, 2025 - 9:46 am

ፊልም አልቀረምንዴ?

Reply

Leave a Comment