0
#FastMereja I ። ሎድሪክ ትሬድንግ ለሃገራችን መልካምድር ሁኔታ ተስማሚ ናቸው ያለውን የያዲ ኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክሎች ከነሙሉ መለዋወጫ እቃዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረቡን ዛሬ መጋቢት 19/2017 ዓ.ም ቦሌ ጃፓን የሚገኘውን ሾው ሩም ባስጎበኘበት ፕሮግራም አስታውቋል።
የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ብሩክ አቢዮት ባደረገው ንግግር እነዚህን የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክሎች ከፍተኛ የማገልገል አቅም ያላችው ባትሪ የተገጠመላቸው ከመሆናቸው ባሻገር አሁን ላይ በሀገራችን ላይ ባለው አረንጓዴ አሻራ ረጅም ጉዞ መጓዝ እንድንችል ከፍተኛ አስተዋጽዎ አላቸው ብሏል።
ሀገራችን በየዓመቱ ለነዳጅ የምታወጣውን ከፍተኛ የዶላር ወጪ በግማሽ የማስቀረት ታላቅ አስተዋጽዎ ያበረክታል ተብሏል።
ሎድሪክ ትሬድንግ የያዲ ኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክሎች በተጨማሪ ስኩተር ለገበያ አቅርቧል።
#FastMereja





1 comment
አብይ ሲነዳ አልተቀረፀም እንዴ ፎቶውስ