#FastMereja I ዳማሪዮስ ፋሽን እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በዓለም አቀፍ ደረጃ በፋሽን፣ በስነ ዉበት (ሜካፕ)፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ ሴኩሪቲ እና በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ለማስተማር አልፎም ስራ አጥነትን ለመቅረፍ አስተምሮ የስራ ዕድልን በማመቻቸት የበኩሉን ለመወጣት ዝግጅቱን አጠናቆ ተማሪዎችን ለመቀበል በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ዛሬ መጋቢት 23/2017 ዓ.ም በተቋሙ በተሰጠ መግለጫ ተገልጿል።
በዳማሪዮስ ተግባር ተኮር የሆኑ ስልጠናዎች እንደሚሰጡ የተቋሙ መስራች ሰናይት ማሪዮ የገለፀች ሲሆን በሀገር ዉስጥ እና ከሀገር ዉጭ የስራ ዕድልን ለሰልጣኞቹ ይመቻቻል ተብሏል።
ከመስከረም ጀምሮ ከLevel 2 ጀምሮ ዓለም አቀፍ በሆኑ ባለሙያዎች ስልጠናዎች እንደሚሰጥ የተገለጸ ሲሆን ሰልጣኞች ስለጠናዉን ካጠናቀቁ በኋላ በተቋሙ ዓቅም መሰረት የፋይናንስ አገልግሎቶች ይመቻቻል ተብሏል።
ከሀገር ዉስጥ እና ከሀገር ዉጭ ከጣሊያን፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ናይጄሪያ፣ ጋና እና አሜሪካ የመጡ መምህራኖች ስልጠናዎችን ይሰጣሉ።
በሜካፕ ትምህርት ከፍል ከMario ሜካፕ ድርጅት ጋር አብሮ ለመስራት ዉል መፈፀማቸውን ገልፀው ከቆዳ ስፔሽሊስት ዶከተሮች ጋር በጥምረት አብሮ ለመስራት ዉል መፈፀሙ ነው የተገለጸው።
አሁን ለ20 ቋሚ ሰራተኞች የስራ እድል የተፈጠረ ሲሆን፣ ከRome Business School ጋር ለተማሪዎች የስኮላርሺፕ ስምምነት ተደርጓል።
ተቋሙ ቦሌ ብራስ የሚገኝ ሲሆን በ1200 ካሬ ሜትር ላይ አርፏል፣ 24 ከፍሎች ሲኖሩት፣ ዘጠኝ የመማርያ ከፍሎች፣ አንድ ቤተ መጽሐፍት ያካተት ተቋም ነው።
አቅም ለሌላቸው ሰልጣኞች ከዳሽን ባንክ እና ከንብ ባንክ ጋር የዱቤ ብድር አገልግሎት ለመስጠት ስምምነት ተፈፅሟል።
ዳማሪዮስ በቀጣይ አምስት አመታት ወደ ዩኒቨርሲቲ ለማደግ እንደሚሰራ ነው የተነገረው።




