0
#FastMereja I “ቴሌብር አዲስ ነገር እስከ ፋሲካ ኤክስፖ 2017 በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተከፈተ።
በቴሌብር አዲስ ነገር እስከ ፋሲካ ኤክስፖ ላይ ከ300 በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ንግድ ተቋማት ምርት እና አገልግሎቶቻቸውን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማህበረሰቡ እንዳቀረቡ የተገለፀ ሲሆን ከንግድ ተቋማት በተጨማሪ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና በልዩ ትኩረት ለአካል ጉዳተኞች በመስጠት የአካል ጉዳተኞች መንደር ተካቷል።
በኤክስፖው ላይ ከኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ጋር በመተባበር የ50 ሚሊዮን ብር ሎተሪ በልዩ ሁኔታ የተዋወቀ ሲሆን አንድ የቤት መኪና፣ የሞባይልና ሞተር ሳይክል በመግቢያ ትኬት አማካይነት በሽልማት መልክ እንደሚወጡ ተገልጿል።
ቴሌብር አዲስ ነገር እስከ ፋሲካ ኤክስፖ 2017 ታሜሶል ኮሙዩኒኬሽን ከታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽን እና ከሊያን ቢዝነስ ግሩኘ ጋር በመሆን እንዳዘጋጁት የተገለፀ ሲሆን ኤክስፖ እስከ ሚያዝያ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ይቆያል።




