#FastMereja I ሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ በየአመቱ የሚቆይ የፍቅር ሳምንትን ሲያከብር ቆይቷል፣ በዝግጅቱ ላይ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የምንግስት ባለስልጣናት ፤ ድርጅት የሀይማኖት አባቶች፣ ታዋቂ አርቲስቶች ፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ነበሩ።
በዚህ የፍቅር ሳምንት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ አካላት ማህበሩ እየሰራ ያለውን ዘርፈ ብዙ የስራ እንቅስቃሴዎች ይጊበኛሉ፣ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን የሚያወሱ የስራ ክንውኖች መምከር ለአብነት ያክልም ጥጥ መፍተል፣ ሽመና፣ ስፌት፣ ማበጠር፣ በድንጋይ ወፍጮ መፍጨት ፣ መውቀጥ እና የመሳሰሉት፣ የሻይ ቡና ፕሮግራሞች፣ ድጋፍ ከሚደረግላቸው ህፃናት ጋር በጋራ በመሆን በመጫወት ፍቅርን ማካፈል፣ ድጋፍ የሚደረግላቸው እናቶች የስራቸው የተለያዩ የእደ ጥበብ ስራዎች ጉብኝት እና ግብይት።
በዘንድሮውም አመትም ከመጋቢት 28/2017 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 5/2017 ዓ.ም ድረስ “በጎ እናድርግ፤ ፍቅራችንን እናካፍል” በሚል መሪ ቃል ለ10ኛ ጊዜ እንደሚከናወን የሙዳይ በጎ አድራጎት ድርጅት መስራች ወ/ሮ ሙዳይ ምትኩ ገልጻለች።
እነዚህን 8 የፍቅር ሳምንት ቀናት በተለያዩ ፍቃደኛ በሆኑ ተቋማት ስም በመሰየም በአብሮነት ለማከናወን የታሰበ ሲሆን ፍቃደኛ የሆኑ ተቋማት ከመጋቢት 28/2017 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 5/2017 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ አንዱን በመምረጥ በውስጣቸው ያሉ የስራ ኃላፊዎችን ፣ ሰራተኞችን እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶችን ጥሪ በማድረግ በሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር ውስጥ የፍቅር ሳምንቱን በጋራ ያከብራሉ፡፡
በመግለጫው ላይ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች ማህበር የፍቅር ሳምንት ላይ ሁሉም የሚዲያ ባለሞያ ተሳታፊ በመሆን የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
ሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር ፤ ሴቶች እና አካል ጉዳተኞችን በልመና ከጎዳና ተዳዳሪነት እና ዝቅተኛ ህይወት በማላቀቅ በራሳቸው እንዲቆሙ ማስቻልን ዋና ዓላማ በማድረግ እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ ሀገር በቀል ግብረ ሰናይ ድርጅት ነው፡፡




1 comment
ከተረጂው በጎ አድራጎት ድርጂቱ በዛ