#FastMereja I ኢትዮጵያ ሪድስ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር መጋቢት 24 እና መጋቢት 25/ 2017 ዓ.ም ለሁለት ቀናት የሚቆይ መርሃ ግብር አዘጋጅቷል፡፡
ዛሬ በመክፈቻ መርሃ ግብሩ ላይ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች፣ በግል እና በመንግስት ዘርፍ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች የታደሙ ሲሆን በዝግጅቱም ከተለያየ ዘርፍ የተወጣጡ ባለሙያዎች የውይይት መነሻ ጥናታዊ ፅሁፎች የሚያቀርቡ ሲሆን በፅሁፎቹም መነሻነት በተሳታፊዎች መካከል የፓናል ውይይትና የሃሳብ ልውውጥ የሚደረግ ይሆናል፡፡
በተጨማሪም የልጆች ንባብ ባህልን ለማሳደግ አስተዋፅኦ ያደረጉ ተቋማትና ግለሰቦች እውቅና የመስጠት መርሃ ግብር ይከናወናል፡፡
ኢትዮጵያ ሪድስ እ.ኤ.አ. 2002 ኢትዮጵያ ውስጥ የተቋቋመ የውጭ ሀገር የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ሲሆን ራዕይውም ሁሉም ሕጻናት በአካልና በስነ ልቦና የማደግ ዕድል እንዲኖራቸው እንዲሁም በትምህርታቸው ጠንካራና በራስ የመተማመን ስሜት ኖሯቸው ማየት ነው፡፡
የድርጅቱ አብዛኛው የፕሮጀክት ትኩረት ልጆች ላይ ሲሆን ይህንንም ለማድረግ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ከ1 ሚሊዮን በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር መጽሐፍትን በተለያየ መንገድ ለተማሪዎች እና ለልጆች ተደራሽ እንዲሆን አድርጓል፡፡





2 comments
ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል ይባል ነበር ዱሮ
This is amazing 👏