0
#FastMereja I የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በልደታ ክ/ከተማ 2 ፍሳሽን ወደ ወንዝን በመልቀቅ ወንዝ የበከሉ ሁለት ተቋማት እያንዳንዳቸው 1,000,000 ብር በድምሩ 2,000,000/ሁለት ሚሊዮን ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን ገለፀ።
ባለስልጣኑ ቢጂ አይ ኢትዮጲያ እና ሞሀ የለስላሳ መጠጦች ማምረቻ ድርጅቶች የሚለቁት ፍሳሽ በተደረገለት የናሙና ምርመራ ወንዝን የሚበክል መሆኑን የተረጋገጠ ሲሆን በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል።
ወንዞችን ከብክለት የፀዱ ከማድረግ አንፃር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በጋራ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎችን በስፋት እየሰጡ መሆኑ ገልፀዋል።
በግንዛቤው መሠረት ተቋማትና ግለሰቦች ከህገወጥ ተግባራቸው ሊቆጠቡ ባለመቻላቸው አስተዳደራዊ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ተመላክቷል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
የፋስት መረጃን የቴሌግራም ገጽ ይቀላቀሉ!
📌 https://t.me/fastmereja
📌 https://t.me/fastmereja

5 comments
ብራቮ ደንቦች
አንድ ተቋም ብትል ይሻላል
እጅግ በጣም አንሷል!! በሀዋሳ ኢንዲስትሪ ፓርኮችን የሚቀጣ መንግስት ጠፋ እንጂ ህዝብ ችግር ላይ ነዉ።
መቼ የጸደቀ የመቅጫ ሕግ ነው??? ይሄኮ ዘረፋ ነው??? የተሰጣቸው ማስጠንቀቂያ የግንዛቤ ማስጨበጫ የታለ???
ቸብችቡ በደንብ!