banner

በ2 ቢሊዮን ብር በሐዋሳ ሐይቅ ዳርቻ እየተገነባ የሚገኘው ሪዞርትና ወተር ፓርክ

#FastMereja I የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በዛሬው እለት በሴንተራል አማረች ሆቴል በ2 ቢሊዮን ብር በላይ እየተገነባ የሚገኘውን ሪዞርትና ወተር ፓርክ ጎበኙ።

የሴንትራል አማረች ሀዋሳ ሆቴል ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍትህ ወልደሰንበት (ዶ/ር) በከተማ አስተዳደሩ በተሰጣቸው ቦታ ላይ ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ሪዞርትና ወተር ፓርክ ግንባታ እያከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቱን በቀጣዮቹ ስድስት ወራት ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንና ከ600 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የስራ እድል እንደሚፈጥርም ገልጸዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጥ፣ የሀዋሳን ሃይቅ ለመዝናኛና ለሌሎች አገልግሎቶች መጠቀም የሚያስችልና ከተማዋን ለኮንፍረንስ ቱሪዝም ተመራጭነትን የሚያሳድግ ነው ብለዋል፡፡

በምልከታው የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ መኩሪያ ማርሻዬ፣ የሲዳማ ክልል ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አንቺንአሉ አሰፋ እና ሌሎች አመራሮችም ተገኝተዋል።





10 comments

Efrem Getachew April 11, 2025 - 5:38 pm

የሌባ ስብስብ ሁላ

Reply
Sidama Daily News Magazine April 11, 2025 - 5:38 pm

በዘራፊዎች እና በወንበዴዎች ላይ የተደረገው ምርመራ 80%በላይ በሕግ የሚያስጠይቅ ተግባር እየፈጸሙ መቆየቱን አንዳንድ ምንጮች እየጠቆሙ ነው።

በዚህ ተግባር ላይ የተሳተፉ አንዳንድ ጥገኛ ባለሀብቶችም እንዳሉ መረጃ እየወጣ ነው። ሠላማዊ ህዝብ ገፎ የጨረሱ ዘራፊ እና ወንበዴ ቡድን በቅርቡ በህግ ቁጥጥር ይውላሉ የሚል በህዝባችን ዘንድ ሙሉ እምነት አለ፤ ህዝባችንም እረፍት ያገኛል።

የተዘረፈው የህዝብ ሀብት ወደ ህዝብ ይመለሳል፤ የሚወሰደው እርምጃ ለሌሎች ክልሎችም ማስተማሪያ የሚሆን እርምጃ እንደሆነም እናምናለን።

ህዝባዊ የለውጥ ትግል ተጠናክሮ ይቀጥላል ✊

Sidama Affairs SA

Reply
Yeroosaa Darribee April 11, 2025 - 5:39 pm

የነራሱን ቤት መቼ ነወየሚመርቀዉ አሜሪካ የገዛውን😳

Reply
አማኑኤል ግርማ April 11, 2025 - 5:40 pm

ቶኪቻው መጣልህ በለው ይሄን መረን

Reply
Ibrahim Abduraman April 11, 2025 - 5:45 pm

ፕሮጀክት ሲያልቅባቸው የግለሰቦችን ሆቴል መጎብኘት ጀመሩ

Reply
Bęñźęmã Mãŋ April 11, 2025 - 5:47 pm

ኮ መዬቶ 😂😂

Reply
Mêqüanint Gödö April 11, 2025 - 5:47 pm

ቶኪቾ ያረጋግጥልን!😍

Reply
Dawit Eyob April 11, 2025 - 5:48 pm

ብልፅግና ጠብቆ ያዋርድሀል

Reply
Abinet Zelalem HM April 11, 2025 - 5:50 pm

እረ ተው … ተው ..ግን ተው!

#ለህጋዊ ደሃው ነው?
ለአርሶ አደሩ ነው?
ለላብ አድሩ
ለመንግስት ስራተኛው ነው
ለጥቃቅን እና አነስተኛው?
እንዳው ለማን ነው?

#ሃላላኪ ግን ደናነው? ጎርጎራስ?
እረ #ጨበራ ጩሩጩራስ
#እንጦጦማ አረጀ…

…

በዚህን ያህል ብር ይሄ ሁሉ ሪዞርት ተገንብቶ መጨረሻው ግን ለማን ነው?
ለየትኛው ህዝብ ነው?

የቸገረን ሰላም
የቸገረን ስራ
የቸገርን ምግብ
የቸገረን ዕውቀት

ምናለ በዚህ ብር #ግድቡን ብጨርሱበት
ምናለ ፋብሪካ ብትከፍቱበት…
ምናለ #ፋይዳ ያለው ነገር ብትሰሩበት

የፈረደበት #ገፅታ ግንባታ!
ምናለ ትውልድ የሚገነባ ነገር ብትሰሩበት

Reply
Ephrem Abate Heramo April 11, 2025 - 5:50 pm

የቀድሞዋን ሐዋሳ ነው የምንፈልገው ያችን ሰላም ያለባትን ፣ በቱሪስቶች የተዋበች ፣ ወጣቶች በስራ ቢዚ የሚሆኑባት ፣ ሁሉም በፍቅር የሚንፈላሰስበትን፣ የሁላችንም ቤት ሃዋሳዬን አምጡልኝ እሷ ናፍቃኛለች ።

Reply

Leave a Comment