banner

በስህተት በባንክ አካውንቷ የገባ 140ሺ ብር ተመላሽ ያደረገችው ፖሊስ

#FastMereja I በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የዝቋላ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት መንገድ ትራፊክ ደህንነት ክፍል ኃላፊ የሆነችው ም/ኢ/ር ሰላም መኮነን ሚያዚያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ረፋድ ላይ በባንክ ሂሳብ ቁጥሯ በስህተት 140,000 /አንድ መቶ አርባ ሺ/ ብር ገቢ ሆነ።

ገንዘቡ የእሷ አለመሆኑን የተረዳችው ም/ኢ/ር ሰላም ለኃላፊዋ በስልክ ወዲያውኑ በማሳወቋ የገንዘቡ ባለቤት ሲጣራ የዝቋላ ወረዳ 01 ቀበሌ ፅፅቃ ከተማ ነዋው ደሳለኝ ኪሮስ መሆኑ ተረጋግጧል።
የዝቋላ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤትም ደሳለኝ ኪሮስን ወደ ቢሮ አስጠርቶ በአደረገው ማጣራት ገንዘቡን ለንግድ ትስስር ላለው ግለሰብ በሞባይል መተግበሪያ ሲያስተላልፍ በስህተት 140,000(አንድ መቶ አርባ ሽህ ) ማስተላለፍን ገልፆ ገንዘቡ ለጠቀሰው ግለሰብ አለመድረሱን ሲያውቅ ተጨንቆ እንደነበር ገልጿል።

ም/ኢ/ር ሰላምም የገንዘቡን ባለቤት ደሳለኝ ኬሮስ መሆኑን ከተረጋገጠ በኋላ 140,000 ብሩን የመለሰች ሲሆን ወጣት ደሳለኝ ኪሮስም ገንዘቡን በማግኘቱ አመስግኗል።

10 comments

Ermi Hailu April 15, 2025 - 6:25 pm

Lemen ene lay aygebam 🤔🤔🤔

Reply
Kefale Genet April 15, 2025 - 6:27 pm

ምነው ሰሞኑን ተመሣሣይ ዜና ሆነ እሳ፣

Reply
Fitsum Yosef April 15, 2025 - 6:28 pm

ሠላም ውድ ኢትዮጵያዊያን ወንድም እህቶች እንዴት ናችሁ ? እኔ የአንድ የ 6 አመት ሴት ልጅ አባት ነኝ ። የምኖረው በክፍለሀገር ከተማ ውስጥ ሲሆን የቀለም ስራ እና ጂፕሠም ባለሙያ ነኝ ። ልጄ ልዩ ፍላጎት የሚያስፈልጋት ስትወለድ በወሊድ ጊዜ በመታፈኗ ምክንያት በተፈጠረባት ህመም ከተወለደች ጀምሮ አሁንም በዚህ እድሜዋም ራሷን ችላ መናገርም መቀመጥም ሆነ መራመድም ምንም ማድረግ የማትችል ልጅ ናት ። የተሻለ ህክምና የፊዝዮቴራፒ ህክምና ብታደርግ እንደእኩያዎቿ ቆማ መሄድ ትችላለች ብለውኛል ሃኪሞች ። እኛ አካባቢ አሁን ላይ ግጭት ስላለ ስራም የለም ማለት ይቻላል ። የማበላትን የማጠጣትን ዳይፐር እና መድሃኒት ለመግዛት ተቸገርኩ ። እባካችሁ አሁን እናንተን የምጠይቃችሁ ለዳይፐር, ለመድሃኒት እና ለህክምናዋ የሚሆን ትንሽ ነገር ብታግዙኝ እያልኩ ነው ። እባካችሁ ከተቻላችሁ ልጄን ከስቃይ እና ከህመም ታደጉልኝ ብድራት በረከቱን ከእግዚአብሔር ታገኙታላችሁ የንግድ ባንክ አካውንቴ 1000081342818 ነው ። ለምታደርጉልኝ ድጋፍ አስቀድሜ አመሠግናለሁ ።

Reply
Øzi Mãn Dz April 15, 2025 - 6:28 pm

እየደበራት ነው የመለሰችው አንተ ፎቶ አነሳሷ😂😂😂😂

Reply
Kassahun Yehualashet April 15, 2025 - 6:29 pm

ለዝች ብላ መልከክከስ የለባትም ጥሩ አረገች😔

Reply
Mekonen Alemu April 15, 2025 - 6:29 pm

ይሄን postየኛ ሰፈር ፓሊሶች ቢያዩት ራሱ ያስሯታል
😫😫😫

Reply
Yeshi Tadesse Yello April 15, 2025 - 6:30 pm

Woda new

Reply
Ete Ete April 15, 2025 - 6:30 pm

ምን ነው ሰሞኑን ሀብታሙ መሳሳት አበዛ
🤲🤲🤲እኛም ጋር ተሳሳቱ

Reply
ሚኩ የእመየ ልጅ April 15, 2025 - 6:30 pm

ወይኔ ያለ ፊት ነው ምታየው እኮ

Reply
Biruktawit Tamirat April 15, 2025 - 6:30 pm

ከመመለስ ውጪ ምን አማራጭ አላት😌😂

Reply

Leave a Comment