0
#FastMereja I የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በመርካቶ እና በመሳለሚያ አካባቢ በመንገድ ሽንት በመሽናት ደንብ ቁጥር 167/2016 የተላለፉ 50 ግለሰቦች እየዳዳቸው 2000 ብር በድምሩ 100,000 /አንድ መቶ ሺህ/ ብር የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡
የከተማ አስተዳደሩ አዲስ አበባን ውብና ፅዱ ለማድረግ ቀንና ማታ እየሰራ ባለበት ወቅት አንዳንድ ሀላፊነት የጎደላቸው ግለሰቦች የተማውን ፅዳት ሲያበላሹ ህብረተሰቡ አካባቢውን ሊጠብቅ እንደሚገባ ተገልፃል።
ባለስልጣኑ በደንብ ቁጥር 167/2016 ላይ ለህብረተሰቡ በተለያዩ አግባቦች ሰፊ የግንዛቤ ስራ መስራቱ የገለጸ ሲሆን ደንብ በሚተላለፉ ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ አንደሚቀጥል አስታውቋል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
#ልዩ_ልዩ

10 comments
ሴቶች አመስግኑ
Good job👏
መንገድ ላይ የህዝብ ሽንት ቤት የለ ሆቶሎች ቆልፈው ነው ሰው የሚስጠቅሙት የት ይሽኑ?
ቁረጡት አልከፊልም😏
መንገድ ላይ የሚሸና ውሻ ነው ሠዎች ብለህ ከኛ ጋር አትደምራቸዉ 😂😂😂
100.000ሺ ቢኖራቸው መንገድ ላይ ኣይሸኑም ባክህ
አሪፍ ነው ይህ ህዝብ ሽንት ቤት ቢሰራለትም አጥር ላይ መሽናት አያቆምም
ብራችን ምን ያህል ዋጋ እንዳጣ ይሄ አንዱ ማሳያ ነው በመሌ ጊዜ እኮ በዛ ከተባለ ሀምሳ ብር ነበር ቅጣቱ
200,000 ብር አልተቀጡም ውሸት
ቅጣቱን የቀጡት ፀረ ኩላሊት የሆኑ ሰዎች ናቸው።