banner

የድምፃዊት የሺ ደመላሽ አዲስ አልበም የመውጫው ቀን ተቆረጠለት

#FastMereja I ድምፃዊት የሺ ደመላሽ ብዙጊዜ የተለፋበትን አልበም ውብ ሰው የተሰኘ የሙዚቃ አልበም ሚያዚያ 12/2017 አመተ ምህረት እንደ ሚወጣ ጠቁማለች፡፡

ድምፃዊት የሺ ደመላሽ “ውብ ሰው” የሙዚቃ አልበም በራስዋ ዩትዮብ ቻናል እና በሌሎች የሙዚቃ መተግበርያ ወደ ህዝብ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ድምፃዊት የሺ ደመላሽ የመጀመርያ አልበምዋ “ቅኔ” አልበም ማድረሷ ይታወሳል በውስጡ 12 የሙዚቃ ክር ሲኖረው ቅኔ ፣ፋኖ፣ ትኩስ እና በራድ ፣ኮከብ፣ ዛሬ፣ መልካም እና ክፊ እና የመሳሰሉት ሲካተቱ በርካታ ከያኒያን ተሳትፈዋል በግጥም ዜማ አብዛኛውን ድምፃዊት የሺ ደመላሽ ስትሆን ቀሪውን ሰለሞን ሙሄ እና አንዱዓለም አባተ ሰርተውታል፡፡

ቅንብር ፡ሮቤል ዳኜ (10) ትራክ፣ እዮብ ፋንታሁን (2) ቀሪው ትራክ ሰርተውታል ሬጌ ሮክ፣ ሬጌ ስልተምት እና ሌሎችም ስልተ ምት ተካተዋል፡፡

ሁለተኛ አልበምዋ “ውብ ሰው” ምን አዲስ ነገር ይጠበቅ ይሁን? ሲወጣ የምንመለከተው ይሆናል፡፡

via ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ

#ኪነ_ጥበብ

1 comment

ፍቅር ያሸንፋል April 16, 2025 - 8:36 am

ዘፈን መች ቸገረን😎

Reply

Leave a Comment