ያንጎ አሽከርካሪዎቹ የሙሉ አረቦን ፕሪሚየም ኢንሹራንስ አገልግሎት ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሥምምነት ከንብ ባንክ እና ንብ ኢንሹራንስ ጋር ተፈራረመ፡፡
#FastMereja I ያንጎ አሽከርካሪዎቹ የሙሉ አረቦን ፕሪሚየም ኢንሹራንስ አገልግሎት ተጠቃሚ የሚሆኑበትን የሦስትዮሽ ሥምምነት ዛሬ ሚያዝያ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ከንብ ባንክ እና ንብ ኢንሹራንስ ጋር ተፈራርሟል።
በኢትዮጵያ በጂቱጂ አይቲ ሶሉሽን ሥር የሚተዳደረው ዓለም አቀፉ የሜትር ታክሲ አገልግሎት ሰጪ ያንጎ፤ በኢትዮጵያ ደረጃውን የጠበቀ ዓለም አቀፍ የራይድ-ሃይሊንግ አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ከሕዳር ወር 2016 ዓ.ም ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ልምድ መሠረት በማድረግ አሽከርካሪዎቹ ደህንነታቸው ተጠብቆ አስተማማኝ አገልግሎት መስጠት የሚችሉበትን ዕድሎች በተለያዩ ጊዜያት በማመቻቸት ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ ከእነዚህም ፕሮግራሞቹ ውስጥ አንዱ በሕግ የተቀመጠውን አስገዳጅ የሦስተኛ ወገን ሽፋን ለከፈሉ የያንጎ አሽከርካሪዎች ተጨማሪ የአረቦን ኢንሹራንስ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ዕድል ማመቻቸት ይገኝበታል፡፡
በዚህም መሠረት ይህንን የያንጎ አሽከርካሪዎች የኢንሹራንስ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል የሦስትዮሽ ስምምነት በዛሬው ዕለት ከንብ ባንክ እና ንብ ኢንሹራንስ ጋር ተፈራርሟል፡፡
ሥምምነቱም የሦስተኛ ወገን ኢንሹራንስ ብቻ የነበራቸውን የያንጎ አሽከርካሪዎች ሙሉ የኢንሽራንስ ክፍያ ለንብ ኢንሹራንስ እንዲከፈል የሚያደርግ ሲሆን፤ በዚህም አሽከርካሪዎች በሥምምነት ሥነ ስርዓቱ ወቅት የጂ ቱ ጂ አይቲ ሶሉሽን ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ቴዎድሮስ መሃሪ እንደተናገሩት፤ የሦስትዮሽ ስምምነቱ የያንጎ አሽከርካሪዎች የሚያጋጥማቸውን ወሳኝ ፈተና በመቅረፍ ተመጣጣኝ እና ተደራሽ የሆነ አጠቃላይ የመኪና ኢንሹራንስ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
“በአሁኑ ጊዜ አብዛኛው የያንጎ አሽከርካሪዎች ለተሸከርካሪዎቻቸው ጥበቃ በሦስተኛ ወገን ኢንሹራንስ ብቻ ይተማመናሉ” ያሉት አቶ ቴዎድሮስ፤ በዚህም ምክንያት አደጋ በሚደርስበት ወቅት ዋና የገቢ ምንጫቸውን ለጥገና በማውጣት ራሳቸውን እና ቤተሰባቸውን ለችግር የሚዳርጉበት አጋጣሚ መኖሩን አንስተዋል።
በመሆኑም የዛሬው ሥምምነት አሽከርካሪዎች በአንድ ጊዜ ሳይሆን በየወሩ አረቦን መክፈል የሚችሉበትን ዕድል የፈጠረ በመሆኑ፤ አሽከርካሪዎች ላይ የሚደርሰውን የገንዘብ ጫናን በእጅጉ ይቀንሳል ተብሎ እንደታመነበት ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም የአረቦን ክፍያውን ከአሽከርካሪዎች ጉርሻ (ቦነስ) ላይ በቀጥታ መቀነስ የሚያስችል አሰራር በመዘርጋቱ፤ አሽከርካሪዎች ያለ ምንም መጨናነቅ የአረቦን ክፍያቸውን ከቦነሳቸው ተቀናሽ በማድረግ መፈጸም ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡
በዚህም ምክንያት በሚያገኙት አጠቃላይ ሽፋን አሽከርካሪዎች ለተሽከርካሪዎቻቸው ጥበቃ እንዲሁም ለቤተሰቦቻቸው መረጋጋት ይሰጣቸዋል ሲሉም ገልጸዋል።
የንብ ባን በበኩላቸው የዛሬዉ ስምምነት ባንኩ ከሚሰራችዉ ዋና ዋና ስራዎች በተጨማሪነት ከ ንብ ኢንሹራንሽ እና ጂቱጂ አይቲ ሶሉሽን ጋር በመተባበር የፋይናንስ አካታችነትን ለማረጋገጥ እና ለአሽከርካሪዎች ምቹ አገልግሎት ለመስጠት የተዘጋጀ ስምምነት መሆኑን አብስረዋል፡፡ የባንኩ ተወካይ እና ቺፍ ኦፐሬሽን ኦፊሰር አቶ ሙሉቀን ደምሴ እንደተናገሩት በስምምነቱ ለታቀፉት አካላት ሁሉን አቀፍ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት ባንኩ ዝግጁ መሆኑን የገለፁ ሲሆን በቀጣይም የመኪና ባለቤቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ ተጨማሪ አገልግቶችን እየተዘጋጁ እንደሆኑ አሳውቀዋል፡፡





1 comment
በሚገባን ብታወሩ ፕሊስ