banner

ፊንቴክ ኢንቨስትመንት ለ4 ዙር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ሊያስረክብ መሆኑን ገለጸ

#FastMereja I ፊንቴክ ኢንቨስትመንት ቀደም ሲል በኦሮሚያ ባህል ማእከል፣ በስካይ ላይት ሆቴል እና በወዳጅነት ፓርክ 250 የኤሌክትሪክ መኪኖች ለደንበኞች ማስረከቡ ይታወሳል። አሁን ደግሞ 200 ቢዋይዲ ሲገልና 58 ኢቱ በድምሩ 258 የኤለክትሪክ መኪኖችን ለማሰረከብ ከጁብቲ ወደ ገላንና ቃልቲ ለማጓጓዝ ዝግጅት መጠናቀቁን የድርጅቱ የስራ ኃላፊዎች ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል በሰጡት መግለጫ ገልጿል።

ፊንቴክ ኢንቨስትመንት የኤለክትሪክ መኪኖች ተፈላጊነትና ፍሰት ከማገዝ አኳያ በንፋስና በፀሐይ ሃይል የሚሰራ ተንቀሳቃሽ የሃይል አማራጭ (Mobile Backup Power)፣ ዘመኑ የዋጁ የቻርጅንግ ስቴሽኖች፤ የመኪና ደህንነት መጠበቅያ ሶፍት ዌሮችና ዲያግኖስቲክ መሳርያዎች፣ የዓቅም ግንባታና የኤለክትሪክ መኪና የቴክኖሎጂ የስልጠና ማእከላት እንዲሁም ሌሎች የኤሌክትሪክ መኪና መሰረተ ልማቶች በመገንባት ላይ እንደሚገኝ ነው የተነገረው።

ፊንቴክ ኢንቨስትመንት ለመኪናው አካል የ5 ዓመት ለባትሪው የ8 ዓመት የአምራቹ ዓለምአቀፋዊ የዋስትና ሰርትፊኬት ለደንበኞቹ ይሰጣል ተብሏል።

ከዚህ ቀደም «ለ12 የሚዲያ ባለሞያዎች በየወሩ መኪና ይሰጣል» ተብሎ የተነገረው በመድረኩ ላይ ከማኔጅመንት ጋር ንግግር ሳይደረግ የተገለጸ ነው በጋዜጠኞቹ ባሳዩት የስራ እንቅስቃሴ አወዳድረን ነው መኪኖችን የምንሰጠው ተብሏል።





Leave a Comment