0
#FastMereja I ከለርፉል ኢሸንት ኦርጋናይዘር 2ኛወን ስታር ዋይድ አዋርድ ማዘጋጀቱን ገለጸ። በበርካታ ዘርፎች ለሐገርና ለወገን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉና እያደረጉ የሚገኙ ኮከብ ተቋማትና ግለሰቦች ይሸለሙበታል።
“ስታር ዋይድ አዋርድ” በንግድ፣ በስራ ፈጠራ፣ በጠቅለለ ኢንቨስትመንት፣ በግብርና፣ በኮንስትራክሽን፣ በባንክ፣ በትምህርት፣ በህዝብ አገልጋይነት፣ በሆቴልና ቱሪዝም ፣ ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ በመጠቀም፣ በእድሜ ዘመን ጋዜጠኛና በሌሎችም በርካታ ዘርፎች ከሐገር መሪዎች እስከ ትልልቅ ኩባንያዎች እውቅና ይሰጣል።
ከለርፉል ኢሸንት ኦርጋናይዘር በኢፌድሪ የንግድ ሚኒስቴር አዋጅ መሰረት የተቋቋመና በሁነት ዝግጅትና ማስተባበር ብሎም የተለያዩ ሁነቶችን በአገር አቀፍና አለም አቀፍ ደረጃ በማዘጋጀት የሚታወቅ ተቋም ነው፡፡




